ሐምሌ 12/2015
ሕወሃት ከ60 እስከ 70ሲ የሚደርስ አዲስ ጦር ትላንት ወደ አካባቢው ማስጠጋቱን ተከትሎ በአካባቢው ከባድ ውጥረት መንገሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ይሄውን ውጥረት ተከትሎም እነ ኮለኔን ደመቀ ዘውዱ የክተት አዋጅ ማወጃቸው ተሰምቷል።
አሁን ገና አይኔ በራልኝ ያለው ሆድ አደሩ የብአዴን ስብስብ ደግሞ ከህወሃት ጋር ጦርነት ውስጥ መግባታችን እውን ሆኗል በሚል ሚሊሻውን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ መጀመሩን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ቆላ ድባና ጎንደር አካባቢ ያሉ ሚሊሻዎችን ጨምሮ በአዊ፣በምስራቅና በምዕራብ ጎጃም ያሉ ሚሊሻዎችም ወደ አካባቢው እየተጫኑ መሆኑን ይናገራሉ።
መቼም እምነት የማይጣልበት የብአዴኑ ስብስብ ይሄን ይበል እንጂ እነ ኮለኔል ደመቀ ግን ለሁሉም የአማራና የአማራ ወዳጅ ለሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የክተት አዋጅ ማወጃቸው ተሰምቷል።
ህወሃትን ሰው በላው ስርአት በጋራ በሚያካሂዱት የአማራ ህዝብን የመጨረስ አጀንዳን የአማራና የትግራይ ህዝብ በጋራ ሆነው ማስቆም ካልቻሉ ነገሩ የከፋ የህዝብ እልቂት ያስከትላል ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
የአማራ ህዝብን በጦርነት፣በረሃብ፣በበሽትና በማፈናቀል ሊጨርስ የተነሳውና በንጹሃን ደም ጭንቅላቱ የሰከረው ግለሰብ በሚጠምቀው ጦርነት ደግሞ ሌላ የሞት ድግስ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
አሁንም ሰአቱ አረፈደምና የአንድም ንጹህ ዜጋ ደም ከመፍሰሱ በፊት ችግሩን ህዝቡ ራሱ እንዲፈታ እድሉ ቢሰጠው ሲሉ የሚማጸኑ በርካቶች መሆናቸውንም ምንጮቹ ሳይጠቁሙ አላለፉም።