በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በእርሻ ስራ ላይ የነበሩ 8 የአማራ ተወላጆች በኦነጉ ገዳይ ቡድን እንደግፋለን በሚሉ የኦሮሞ ጽንፈኞች በግፍ መገደላቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በወቅቱ ጥቃቱ ሲፈጸም በማሳቸው ላይ የነበሩት 9 የአማራ ተወላጆች መሆናቸውን የሚናገሩት ምንጮቹ ከተገደሉት 8 ንጹሃን የአማራ ተወላጆች በተጨማሪ አንድ ሰው ቆስሎ መትረፉን ተናግረዋል።
በተደጋጋሚ ገዳይ ቡድኑን በመተማመን አብሯቸው የኖረውን የአማራ ህዝብ ሲያስፈራሩና ሲያሳድዱ የቆዩት እነዚሁ የጽንፈኛ ስብስቦች አሁን ደግሞ አይን ወዳወጣ ዘር ማጥፋት ተሸጋግረዋል ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።
እንዲሁም ወደ ምንጃር ለስራ ሔዶ የነበረ ወጣት በዚሁ ስብስብ መገደሉን ተናግረዋል።
ከእሱ ጋር የነበሩት ጓደኞቹ በህይወት ቢተርፉም የጓደኛቸው አሟሟት ግን እስካሁን እንቅልፍ እንደነሳቸው ነው ምንጮቹ የሚናገሩት።
የአካባቢው ማህበረሰብም ያለውን አሰባስቦና ተሽከርካሪ ተከራይቶ አስከሬኑን ወደ ትውልድ ስፍራው ወደ ደብረወርቅ መላካቸውንም ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት በጎንደር የሃሙሲት ወረዳንና አካባቢውን የተቆጣጠረው የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ዛሬም በተለያዩ አቅጣጫዎች ከዚሁ ገዳይ ቡድን ጋር አንገት ላንገት ተናንቆ እንደሚገኝም ምንጮቹ ገልጸዋል።
በአብዛኞቹ የአማራ ክልል አካባቢዎች የኦህዴዱ ብልጽግና አጠናክሬዋለሁ ብሎ የሚያስበውን መዋቅር በመበታተንም በርካታ አካባቢዎችን እየተቆጣጠረ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በወሎ ግንባርም ወግዲ ላይ የምስራቅ አማራ ፋኖ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሊገለው የመጣውን ስብስብ ማራገፍ ብቻ ሳይሆን በርካታ የቡድንና የግል መሳሪያዎችን በክብር እንደተረከበም ምንጮቹ በአድናቆት ይናገራሉ።
በሰሜን ሸዋ ሸዋሮቢት ላይም የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር መራገፉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
ትላንት የመጀመሪያውን ሽንፈት ከተከናነበ በኋላ ዳግም ጥቃት ለመፈጸም የጀመረው ይሄው የገዳዮች ስብስብ በፋኖ ህዝባዊ ሃይልና በህብረተሰቡ ጥምረት ከባድ ውጊያ ገጥሞታል ብለዋል።
በሁሉም አቅጣጫ ጭንቅላቱን በሆዱ በቀየረው የጄኔራሎች ስብስብ የፈለገውን ቢለፋም ቆርጦ ከተነሳው ህዝባዊ ሃይል የሚደርስበትን ሽንፈት መቋቋም አልቻለም ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች አስታውቀዋል።
ደብረታቦርን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የአማራውን ትጥቅ አስፈቱ ተብለው ከሚላኩት የሚሊሻና የፖሊስ አባላት ደግሞ አብዛኞቹ ከነመሳሪያቸው ህዝባዊ ሃይሉን እየተቀላቀሉ መሆኑን ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁሉም አቅጣጫ አማራውን መሪ ለማሳጣት እየጣረ ያለው ሰው በላው ስርአት አዲስ የፍርድ ቤት ማዘዣ አስወጥቶ አርበኛ ዘመነ ካሴን ለማፈን እንቅስቃሴ መጀመሩን ምንጮቹ ይናገራሉ።
ዘመነ ካሴ ግን ቁርጥ ያለ መልሱን መተው እንዲሞክሩትና ሁሉንም ነገር በሶስት ቀን አፈራርሶ እንደሚያሳያቸውን ቁልጭ አድርጎ ነግሯቸዋል ብለዋል ምንጮቹ።
Comentários