ከባህርዳር በሞጣ ወደ አዲስ አበባ በ18 ኮብራ ተሽከርካሪዎች የባአዴኑ ባለስልጣናት ከነቤተሰቦቻቸው ሲጓጓዙ ማደራቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ዛሬ ለሊቱን ሲጓዘ ያደረው የሆድ አደሩ የብአዴን ሹማምንት በቀጥታ አዳነች አበቤ ወዳዘጋጀችለት የኪራይ ቤቶች ቤት የሚገባ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በአንጻሩ ደግሞ ከየወረዳውና ከየዞኑ ሸሽቶ የባህርዳር ሆቴሎችን ከነቤተሰቦቹ ያጨናነቀው አመራርና ካድሬ ደግሞ በአስቸኳይ ወደ መጣህበት ተመለስ የሚል ትእዛዝ ከብአዴኑ የበላይ አመራር ማስጠንቀቂያ እንደደረሰውም ተናግረዋል።
ትላንት ስብስባ ብሎ የጠራቸው አካል ወደየወረዳቸውና ወደየቀበሌያቸው ተመልሰው ሁኔታዎችን እንዲያረጋጉ መመሪያ እንደተሰጣቸውም ገልጸዋል።
ነገር ግን ሸሽቶ የመጣው አመራር የኦህዴዱ መከላከያም ሆነ ሚሊሻው ለእኛ ጥበቃ እስካላደረግልን ድረስ በምን ዋስትና ነው የምንመለሰው በሚል አሻፈረኝ ማለቱንም ገልጸዋል።
ከባድ ውዝግብ እርስ በርስ ቢፈጠርም በጉዳዩ ላይ ግን ምንም አይነት መፍትሄ ሳይሰጥ ሸሽቶ የመጣው አመራር ወደ ያዘው ሆቴል መመለሱን ተናግረዋል።
አብዛኞቹ አካባቢዎች እየተቆጣጠረ ያለው የፋኖ ህዝባዊ ሃይል እስኪያውጅ ነው እንጂ ብአዴን የሚባለው ስብስብስ ሊያከትምለት የቀረው በጣት የሚቆጠር እድሜ ነው ሲሉም እውነቱን ተናግረዋል።
የሚያሳዝነው ይላሉ ምንጮቹ አስቀድሞም መቀመጫውን በአዲስ አበባ ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው የብአዴኑ የላይኛው ሆድ አደር ስብስብ ራሱንና ቤተሰቡን በተለያየ አቅጣጫ እያሸሸ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሌላውን አመራር ተመለስ ማለቱ በራሱ ከባድ ውጥረትን አንግሷል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
Comments