ሐምሌ 13/2015 በቤንሻንጉል በኦህዴዱ ኦነግ በእርቅ ስም ገብቶ የነበረው የጉምዝ ታጣቂ ቡድን ተመልሶ ጭካ መግባቱን ነዋሪዎቹ ገለጹ።
- Ethio 360 Media 2
- Jul 20, 2023
- 1 min read
በቤንሻንጉል በኦህዴዱ ኦነግ በእርቅ ስም ገብቶ የነበረው የጉምዝ ታጣቂ ቡድን ተመልሶ ጭካ መግባቱን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ግልገል ሲቀለብና በገዳዩ ስርአት ሲሰለጥን የቆየው ይሄው ገዳይ ቡድን ጫካ መግባቱን ተከትሎ በግልገልም ሆነ በማንዱራ ከባድ ስጋት ሰፍኗል ብለዋል።
ይሄንን ገዳይ ቡድን የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል ከቦታል የሚል ፕሮፓጋንዳ ለማህበረሰቡ እንዲነዛ ከተደረገ በኋላ ለሊቱን ከአካባቢው እንዲወጣ ተደርጓል ብለዋል።
ቁጥራቸውን ለማጣራት ባይችሉም ብዛት እንዳላቸው ግን ማወቅ መቻላቸውን ይናገራሉ።
ዋናው ተደራጅቶ ሰልጥኖ እንዲላክ የተደረገው ለሌላ ሳይሆን ንጹሃንን እንዲገል ለማድረግ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
እንኳን ይሄ አራጅ ቡድን ተጨምሮ ተለቆ አይደለም አስቀድሞም ቢሆን ከቤት ወቶ በሰላም ለመመለስ የነበረው ስጋት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑንም ሳይገልጹ አላለፉም።