በጋምቤላ ትላንት አምስት የአኝዋክ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች መገደላቸውንና አስከሬናቸው ተቆራርጦ መጣሉን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
በየቀኑ ሰዎች የሚገደሉት በአካባቢው የጸጥታ ሃይልና ክልሉን የሚያስተዳድር አካል አለ በሚባልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ይላሉ።
አሁን ላይ ጋምቤላ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግድያ የምናውቀው በፊል እንጂ በእውነተኛው ህይወት አይመስልም ሲሉ ግፉን ያናገራሉ።
መሳሪያ የታጠቀው ይሄው ሃይል ከጋምቤላ ከተማ በ15 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ 5 ሰዎች ተገለው ሬሳቸው እንዲቆራረጥ ተደርጓል ብለዋል።
ትላንት የአንዋር ተወላጆች የሚኖሩበትን አካባቢው የወረረው አካል ከገደላቸው ሌላ 5 ሰዎችን ማቁሰሉንም ገልጸዋል።
የተገደሉትን ወገኖቻቸውን በአይን እንዳዩ የሚናገሩት ነዋሪዎቹ እስካሁንም የት እንደደረሱ የማይታወቁ ሶስት ወገኖቻቸው እንዳሉ ተናግረዋል።
ከዛም አልፎ ከሌላው አካባቢው ባገኙት መረጃም ሌሎች አስከሬኖች ወድቀው መገኘታቸውንም አንስተዋል።
እስካሁን የሚገድለው ንጹህ ዜጋ ቁጥር ባይታወቅም ይሄ ግድያ የሚፈጸመው ግን ከውጪ በሚመጣው ታጣቂ ቡድንና በኦነግ ገዳይ ቡድን በጋራ ነው ብለዋል
ግድያው ሲፈጸም በአዋጅ ተነግሮና በማስታወቂያ ሁሉ እየተነገረ ስለሆነ ለማንም አቤት ማለት አይታሰብም ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ይሄ ሁሉ ግድያና ማሰቃየት ደግሞ አላማው የአኝዋክ ተወላጆችን ማባረር ነው ሲሉ ያስቀምጣሉ።
ክልሉን የሚያስተዳድረው የአኝዋክ ተወላጅ ነውና ስልጣኑን ያስረክብ የሚል አይን ያወጣ አካሄድ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 የገለጹት።
Comments