በደቡብ ወሎ የወግዲ ወረዳ ነዋሪዎች በኦህዴዱ ሃይል እየተገደሉ ሲሆን የሸዋ ሮቢት ህዝብ ለመጨረስ ደግሞ አዲስ ሃይል ወደ አካባቢው እየገባ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ከኦህዴድ በላይ ኦህዴድ ነን በሚለው ገዳይ ቡድን የወግዲ ወረዳ ንጹሃን ዜጎች በቅጠል እንዲረግፉ እየተደረገ ነው ይላሉ።
እስካሁንም በየአካባቢው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውንም ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።
አሁንም ቤት ለቤት ችምር ግድያውን የቀጠለው ይሄው ሃይል የባንክ ሰራተኞች ጨምሮ ያገኘውን ሁሉ በማሳደድና በመግደል ላይ መሆኑን አመልክተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በሆድ አደሩ የብአዴን አመራር የሚታዘዘው ሚሊሻና የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል በጋራ በመሆን ወደ ሸዋ ሮቢት እያቀኑ መሆኑን ይናገራሉ።
ከ15 በላይ በሚሆኑ ተሽከራካሪዎች ተጭኖ እየተጓዘ ያለውን ይሄንን የገዳዮች ስብስብ ቦታው ላይ ሳይደርስ ከመንገድ ላይ ማስቀረት ካልተቻለ በቀር የተደቀነው አደጋ ከባድ ነው ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል።