የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት መስጠቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ታዋቂዋ አርቲስት እጅጋየሁ ሺባባው ጂጂ፣ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማስተዋወቁ በኩል ላበረከተችው ታላቅ አስተዋፅኦ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬቱ አበርክቶላታል ብለዋል።
ዩኒቨርስቲው ባካሄደው የተማሪዎች የምረቃ ስነስርአት ላይ ነው ለአርቲስቷ የክብር ዶክተሬቱን ያበረከተላት።
ሽልማቱን በወላጅ እናቷ በኩል የተቀበለች አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ)የተሰጣትን የክብር ዶክትሬት በታላቅ ደስታ መቀበሏን ባለችበት ቦታ ባስተላለፈችው መልዕክት አስታውቃለች።
ለሽልማት መታጨቷ በራሱ እንዳስገረማት የተናገረችው ጂጂ በዚህ ደግሞ እሷ ብቻ ሳትሆን ደስታቸውን አብረው ሆነው በገለጹ ኢትዮጵያውያን ስምም ምስጋናዋን ማቅረቧንም ገልጻለች።
תגובות