ሐምሌ 20/2015በጎንደር ደንቢያና አካባቢው ትላንት የነበረው ጦርነት በተወሰነ ደረጃ መረጋጋቱን ገለጹ።
- Ethio 360 Media 2
- Jul 27, 2023
- 1 min read
በጎንደር ደንቢያና አካባቢው ትላንት የነበረው ጦርነት አሁን ላይ በተወሰነ ደረጃ መረጋጋቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ነገር ግን አሁን የገዳዩ ስርአት ሃይል አካባቢው ላይ መኖሩን የሚናገሩት ምንጮቹ ምናልባትም ይሄው ቡድን አዘናግ በንጹሃን ላይ ጦርነት ሊክፍት ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
አሁን ላይ ደንቢያ እና ዙሪያው ተኩስ ቢቆምም ይሄው ገዳይ ቡድን ግን ከሰራባ ጭልጋ ሃይሉን እያጋዘ መሆኑን ተከትሎም ሰቀልት አይምባ ላይ ሕዝቡ መንገድ መዝጋቱን ተናግረዋል።
ከወረታ ለተጫነው የሰው በላው ስረት ሃይልም ማክሰኝት ላይ ህዝቡ መንገድ ዘግቶ ጠብቆታል ብለዋል።
አሁንም የፋኖ ህዝባዊ ሃይልና ህብረተሰቡ በጋራ የሞት የሽረት ትግል እያደረገ ባለበት ሰአት ደግሞ የራሳቸውን ህዝብ ለማስመታት እየለፉ ያሉ አመራሮች መኖራቸውን በፎቶ በማስደገፍ ጭምር አመልክተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ፋኖ ጋሸና ከተማን ሲቆጣጠር አብዛኛውም የገዳዩን ስርአት ሃይል ደግሞ ምርኮኛ ማረጉን አስታውቀዋል::
በተያያዘ ዜና አማራ ሳይንት ላይ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል በለጩማ ላይ ምስግ ቆፍሯል በሚል ብቻ አካባቢው በከባድ መሳሪያ እየተደበደበ መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
የገዳዩ ስርአት ሃይል በከባድ መሳሪያ ምሽግ ሲደበድብ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ደግሞ በጎን በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የገዳዩን ስርአት ሃይል ከነመሳሪያው ማርኮታል ብለዋል።