ኢትዮጵያን አስተዳድራለሁ ብሎ የሚያስበው አካል ሰዎችን ለማጥበድ የሚያስችሉ ጥቃቅን መሳሪያዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በገፍ እያስገባ መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገለጹ።
እነዚህ መሳሪያዎች እንደ ቁልፍ መያዣና በእጅ በቀላሉ የሚያዙ ወይንም ልብድ ላይ መለጠፍ የሚችሉ ቀላል እቃዎች መሆናቸውን ይናገራሉ።
አሁን ላይ እንዲያውም ከተወሰነ ድርጅት ጋር በመስማማት በፋኖ ስም የቁልፍ መያዣ አሳተምን እስከማለት የሚደርስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ይናገራሉ።
እነዚህ እቃዎች በዋናነት አገልግሎት ላይ የሚውሉት የሚፈለጉና ለስርአቱ አደገኛ ናቸው የሚባሉ ሰዎችን በቀላሉ ለማጥመድ ነው ይላሉ።
ነገር ግን እነዚህ ዲቫይሶች በገፍ እያስገባ ያለው አካል ህብረተሰቡ እንዳይነቃም በየገበያው እንዲበተኑ እንደሚያደርግም የውስጥ ምንጮቹ አስቀምጠዋል።
ምናልባትም ይሄ መሳሪያ በቀላሉ የሚበተነው በአማራ ክልል በተለይ ደግሞ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ይንቀሳቀስባቸዋል በሚባሉ አካባቢዎች ሊሆን ይቻላል ሲሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ሰውን አድኖ ከመያዝ ይልቅ እነዚህን የስለላ እቃዎች ህዝቡ በብዛት እንዲጠቀምባቸው በማድረግ በቀላሉ የሚፈለጉ ሰዎችን ማጥመድ የሚለው ዋናው አጀንዳ መሆኑንም አንስተዋል።
የሰው በላው ስርአት በገፍ እየገዛ እያስገባ ያለውን ይሄንን መሳሪያ የሚጠቀም ሰው የዚሁ አካል ተጠቂ ይሆናል ሲሉም ያስቀምጣሉ።
ይሄን ቁልፍ መያዣ ወይንም ተመሳሳይ እቃዎችን የሚጠቀምን ግለሰብ በደቂቃ ውስጥ ማጥመድ እንዲቻል ተደርጎ መሰራቱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ምናልባትም እንደህዝብ ተደቀነበትን የአፈና መንገድ በዘዴ ማለፍ ካልቻለ ነገሮች ሁሉ ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ የተደቀነውን አደጋ ተናግረዋል።
Comments