top of page

ሐምሌ 20/2015 የደቡብ ክልል ዋና ከተማን በመወሰኑ ጉዳይ ላይ ከባድ ውዝግብ ተፈጠር!

!


የደቡብ ክልል ዋና ከተማን በመወሰኑ ጉዳይ ላይ ከባድ ውዝግብ መፈጠሩን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።አስቀድሞ የክልሉ ዋና ከተማ አርባ ምንጭ ይሆናል በሚል ከዛሬ 8 ወር በፊት ተወስኖ እንደነበር ያስታውሳሉ።የቱሪዝም ከተማ ነች የምትባለው አርባምንጭ ዋና ከተማ ናት በሚል የተማመነው አመራር በአካባቢው ቦታ ወስዶ ቤት እስከመገንባት መድረሱንም ተናግረዋል።


ነገር ግን አሁን ያ ሃሳብ ተቀይሮ የክልሉ ዋና ከተማ ወላይታ ላይ ነው መሆን ያለበት የሚል አዲስ አጀንዳ ተይዞ ብቅ ማለቱን ጠቁመዋል።


ዋና ከተማውን ወደ ወላይታ ማምጣት የተፈለገው ደግሞ ህዝቡ አሁንም የክልል እንሁን ጥያቄውን አክርሮ በመያዙ ነው ብለዋል።


ብርቱካን ሚደቅሳ የብልጽግናውን ካድሬ አሰባስባ በዞኑ ህዝበ ውሳኔ ተካሂዷል በሚል ያካሄደችው የውሸት ምርጫም ውጤት የህዝቡን አቋም ሊያስቀይር አልቻለም ሲሉ የሰራችውን ውንብድና አጋልጠዋል።


አሁን ታዲያ የደቡን ክልል ዋና ከተማ ወላይታ ይሁን በሚል የህዝቡን ቀልብ ለመሳብና አጀንዳ ለማስቀየር እየሞከረ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ወላይታ ላይ ይሁን በሚል አዲስ አጀንዳ የመጣበት ሌላኛው ጉዳይ ግን ህዝቡ አሁንም አመጹህ ከቀጠለ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኘው የሰው በላአ ስርአት ሃይል እርምጃ ይወስዳል በሚል እምነት ስለተጣለበት ነው ሲሉ ምንጮቹ አስምረውበታል።


የወላይታ ህዝብን ቁጣ ለማፈን እየሰራ ያለው አካል ዋና ከተማውን አርባ ምንጭ ላይ ካደረገ ደግሞ ሌላ አደጋ ይደርስብኛል በሚል ስጋት መሆኑን ያነሳሉ።


ምክንያቱም ዋና ከተማው አርባ ምንጭ ላይ ከተደረገና በድንገት አመጽ ከተፈጠረ ዋና መንገዱን ሁሉ በመዝጋትና ወዴትም እንዳያልፉ በማድረግ ነገሩን ሁሉ ያበላሹታል በሚል ስጋት ላይ በመውደቁ ነው ብለዋል።


ስለዚህ በቀላሉ የወላይታ ህዝብን አፍኜ ሁሉንም እንደፈለኩ እገዛለሁ ብሎ የሚያስበው አካል ውና ከተማውን ወደዛ አመጣለሁ ማለቱ ደግሞ በራሱ ካድሬ ሳይቀር ውዝግብ ውስጥ መክተቱን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ከዚህም በላይ ምናልባትም ዋና ከተማው እኛ ጋር ይሁን እኛ ጋር ከሚለው ውዝግብ ጋር ተያይዞም ምናልባት ሌላ ችግር ሊፈጠር ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።


በተለይ የክልል እንሁን ጥያቄ በማንሳቱ ብቻ ከፍተኛ እንዲደረግበት የተደረገው የወላይታ ህዝብ አሁን ደግሞ ዋና ከተማውን አንተ ጋ ልናመጣ አንው በሚል ሌላ የሞትና የአፈና ድግስ ተዘጋጅቶለታል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Comments


bottom of page