እየተፈጠረ ያለው ነገር በጣም አሳሳቢ ነዉ የሚሉት የውስጥ ምንጮቹ ቀደም ሲል ኢምባሲዎች በሙሉ የሚጠበቁት በፌደራል ፖሊስ እንደነበር ያነሳሉ።
ነገር ግን አሁን ላይ በሙሉ ሰራዊቱ መሳሪያውን እንዲያወርድ ተደርጎ ኤምባሲን ያህል ነገር በዱላ እንዲጠበቅ ተደርጓል ብለዋል።
አዲስ አበባን በገዳይ ቡድን ያስወረረው አካል ኤባሲዎችን በዱላ እንዲጠበቁ እስከ ማድረግ ሲደርስ አንድም አካል ተው ሊለው አልቻለም ብለዋል።
ይሄ የፌደራል ሃይል የሚባለው ስብስብ አስቀድሞም ጥበቃው ማማ ላይ ስለሆነና ዙሪያውን ሊፈትሽ የሚወርደው ምሽት ላይ በመሆኑ ምናልባትም መሳሪያ ሳይሆን ዱላ ይዞ እንደሚጠብቅ ኤምባሲዎች ላያስተውሉት ይችላሉ ሲሉ ስጋቱን አስቀምጠዋል።
በቅርበት ሆነው ይሄንን ጉዳይ የሚመለከቱት የውስጥ ምንጮቹ ምናልባትም ይሄ መረጃ ቢወጣ በድብቅ እየተሰራ ያለው ወንጀልን በጊዜው ማስቆም ይቻላል ሲሉ እየተሰራ ያለው አይን ያወጣ ቀውስ አጋልጠዋል።
የየኤምባሲው ሰራተኛ መውጣትን ተከትሎ ግቢው ውስጥ ዱላ ብቻ ይዞ የሚቀሳቀሰው ይሄው የፌደራል የተባለው ሰራዊት አደጋ ቢፈጠር ምን ሊያደርግ እንደሚችል የሚያውቁት እሱና ትጥቅ ያስወረዱት አለቆቹ ብቻ ናቸው ሲሉ የውስጥ ምንጮቹ ገልጸዋል።