በኦሮሚያ ክልል በተለይ በወለጋ አካባቢ ያለ የኦሮሞ ተወላጅ ሁሉ ውድ ንብረቱንም ሸጦ ቢሆን መሳሪያ እንዲገዛ አዲስ መመሪያ መውረዱን በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ለኢትዮ 360 ገለጹ።
የሰው በላው ስርአት የወረደው መመሪያ በተለይ በምስራቅ ወለጋ፣በሆሮጉድሩና በአካባቢው ያሉ የኦሮሞ ተወላጆች ሁሉ መሳሪያ እንዲገዙ አዲስ መመሪያ ወርዷል ብለዋል።
አማራው ራሱ በገዛው መሳሪያ ነው ራሱን እየተከላከለ ያለው ስለዚህ እሱንም ማስለቀቅ ያልቻላችሁት ለዛ ነው በሚል ቅስቀሳ እየተደረገላቸው መሆኑን ያነሳሉ።
እነሱ መሳሪያውን ከገዙ በኋላ ደግሞ ስልጠናውም ሆነ ግብአቱ ከዚሁ የገዳዮች ስብስብ እንደሚሟላለት ቃል ተገብቶለታል ብለዋል።
ከሐምሌ 21 ጀምሮም ስልጠና መሰጠት መጀመሩንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ከሳምንት ወይንም ከሁለት ሳምንት በኋላ አማራውን መጨፍጨፍ ይጀመራል የሚሉት የአማራ ተወላጆቹ ያለው እንቅስቃሴ ከበፊቱ ለየት ያለ በመሆኑ አስፈሪ ነው ሲሉ ገልጸውታል።
ሊፈጸም የታሰበውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ሁሉም ወለጋ ካለው የአማራ ተወላጅ ጎን በመቆም እንዲያስቆምለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።