top of page

ሐምሌ 25/2015 የልደታ ፍርድ ቤት ችሎት ዛሬም በተቃውሞ ሲናጥ መዋሉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



በዶክተር ወንደሰን የክስ መዝገብ ያሉ የህሊና እስረኞችን ጉዳይ ለማየት የተሰየመው የልደታ ፍርድ ቤት ችሎት ዛሬም በተቃውሞ ሲናጥ መዋሉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



የህሊና እስረኞቹ ዳኛዉ የፖለቲካ ወገንተኛ ናቸው ይነሱ፣ከኦህዴድ ዳኛ ፍትህ አንጠብቅም በሚል ያነሱት ቅሬታ ችሎቱን በተቃውሞ ሲንጠው መዋሉንም ምንጮቹ አመልክተዋል።



የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሐምሌ25/2015 ዓ.ም በእነ ዶ/ር ወንደሰን መስከረም አበራ የክስ መዝገብ የቀረቡ 28 ተከሳሾች ችሎት ገና ከጅምሩ በቦታው የተገኙ ቤተሰብ እና ደጋፊዎቻቸው ወደችሎት እንዳይገቡ በመከልከልና በጣም ለጥቂቶች በመፍቀድ የተጀመረ መሆኑን ያነሳሉ።



ቀጠለና ሁሉም የህሊና እስረኞች በጋራ የመሀል ዳኛዉ ይነሳልን ጥያቄያቸውን በጽሁፍ ሊያቀርቡ ሲሞክሩ መከልከላቸውን ተከትሎም የህሊና እስረኞቹ በፖለቲካ ወገንተኛው በኦህዴዱ ዳኛ አንዳኝም ከሱም ፍትህ አንጠብቅም በሚል ችሎቱን በተቃውሞ እንዲናጥ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።



ይነሳ የተባለው ዳኛ ደግሞ ጥያቄያቸውን በማስረጃና በቃል እንዲያቀርቡ ማዘዙን አንስተዋል።


የህሊና እስረኞቹ ግን እኛ ጥያቄያችንን የሚዲያ አካላትና ህዝቡ ብሎም ቤተሰቦቻቸው ሁሉንም ነገር እንዲያውቁ በጽሁፍ እንጂ በቃል እንደማያቀርቡ በግልጽ ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል።


የተከሰስነው በአማራነታችን ነው ያሉት የህሊና እስረኞቹ በኦህዴድ ዳኛ አለመዳኘት ደግሞ መብታቸው መሆኑን በመጥቀስ ከባድ ተቃውሞ በችሎቱ መፈጠሩንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።



ከዚህም ጋር ተያይዞ በችሎቱ ምንም ክርክር ሳይደረግ መቋረጡንና ቀጣዩ ቀጠሮን በማራዘም ለጥቅም 15/2016 እንዲሆን ተደርጎ ችሎቱ መበተኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page