ለመምህራኑ የተቀመጠላቸው ምርጫ በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምሀር ቤቶች ወይንም ከአዲስ አበባ ተሰርቆ በተወሰድውና ሸገር የሚል ስም በተሰጠው አካባቢ ማስተማር የሚል መሆኑን አንስተዋል።
ምርጫቸውን የሚያሰፍሩበት ቅጽ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው መምህራኑ አስቀድመው ግን ውሳኔያቸውን አዘጋጅተው እንዲጠብቁም እንደተነገራቸው ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ወደ ተሰረቀው አካባቢ ለሚሄዱ መምህራን ደግሞ መሬት እስኪሰጣቸው ድረስ የቤት ኪራይ 3ሺ ብር ይሆንላችኋል በሚል ድለላ መጀመሩንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ነገር ግን ለመምህራኑ ይሄ ምርጫ ሲቀመጥ ሸገር በሚል ተሰርቆ በተወሰደው አካባቢ ለሚማረውና ቁጥሩ ከ80 እስከ 90 በመቶ ስለሚሆነው የአዲስ ተማሪ ግን የተባለው አንዳችም ነገር የለም ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
ቀጣዩ የትምህርት ዘመን አስፈሪ ነው የሚሉት የኢትዮ 360 ምንጮች ሁሉንም ለኔ የሆነው ስብስብ ትውልድን በመግደል ተወዳዳሪ የማይገኝነት መሆኑን በግልጽ እያስመሰከረ መሆኑን ምንጮቹ ሳይጠቁሙ አላለፉም።