በአማራ ክልል ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎትን ያቋረጠው የሰው በለው ስርአት ያሰማራው ገዳይ ቡድን በጎንደር ዩኒርስቲ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በፈጸመው ጥቃት ሶስት ተማሪዎችን ሲገድል ከ20 በላይ ማቁሰሉን የህዝባዊ ሃይል አባላቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ጉዳት ከደረሰባቸው አብዛኞቹ ደግሞ ለ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲው ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች መሆናቸውን አባላቱ ተናግረዋል።
ዩኒቨርስቲውን እንደመጠለያ አድርጎት የነበረው የዚሁ ገዳይ ቡድን አብዛኛው ተደምስሷል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ገዳዩ ቡድን በሚገባው ቋንቋ ዋጋውን አግኝቷል የሚሉት የህዝባዊ ሃይሉ አባላቱ ትላንት ደብረታቦር ላይም በተመሳሳይ መልኩ ይሄ ገዳይ ቡድን ዋጋውን አግኝቷል ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል።
አሁንም ጎንደር ከተማ ላይ ያለው ሃይል መከበቡንና የቆሰለውም ሆነ የሞተው ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
አሁን ላይ ዋና የሚባሉ መንገዶች መዘጋታቸውን የህዝባዊ ሃይል አባላቱ በሚቻለው ነገር ሁሉ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ስራ እየተሰራ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
አሁን ላይ ከፋኖ ህዝባዊ ሃይሉ ጋር የቀድሞ የመከላከያም ሆነ በተለያየ መስክ ላይ ያሉ ሁሉ ተሳታፊ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።
አሁን ላይ በክልሉ ያለው ትግል የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን የህዝብ ትግል ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በየቦታው የሚሰነዘረውን ጥቃትም ህብረተሰቡ ቀድሞ በመመከት ትግሉ ህዝባዊ መሆኑን እያሳየ ነው ሲሉም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።