top of page

ሐምሌ 27/2015 የአማራ ሕዝባዊ ሃይል በርካታ ከተሞችን እየተቆጣጠረ መሆኑን አስታወቁ።


የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ደብረወርቅና ሞጣን ጨምሮ በርካታ ከተሞችን እየተቆጣጠረ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።


ለሊቱን በሙሉ ኢንተርኔት በማቋረጥና በአንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል እንዳይኖር በማድረግ ጭምር ጥቃት ለመሰንዘር ያሰበው ገዳይ ቡድን በየትኛውም ግንባር ሊሳካለት አልቻለም ብለዋል።


በደብረወርቅ ጥቃት እከፍታለሁ ብሎ የተነሳው ሃይል በህዝባዊ ሃይሉ አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ ከተማውን ለባለቤቶቹ አስረክቧል ሲሉም ምንጮቹ አመልክተዋል።


በደጋ ዳሞት ሆነ በደምበጫ ጅጋ የተካሄደውን ጦርነት ያገዘው የፍኖተ ሰላም እና የደብረ ማርቆስ ህዝብ ደግሞ መንገድ በመዝጋት አንድነቱን አሳይቷል ብለዋል።


ሸዋ ሮቢት ላይ አሁንም ንጹሃንን በአደባባይ መግደሉን የቀጠለው የገዳዩ ቡድኑ ሃይል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊቱንም ወደ አካባቢው ማጋዝ መቀጠሉን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በሔሊኮፕተር በመታገዘ የባህርዳርንና አካባቢውን ህዝብ ለማሸበር የሞከረው አካል ትላንት ማምሻውን የባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 አካባቢን በተኩስ ሲያምስ ማምሸቱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ትላንት ከምሽቱ 4 ሰአት ጀምሮ በደብረ ብርሃንና አካባቢን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ያደረገው አካል ከለሊቱ 6 ሰአት ጀምሮ የገዳዩን ሃይል በሶስት ተሽከርካሪ ሙሉ ጭኖ በማስገባት ደብረብረሃን ወልዶ መጣያ ትምርት ቤት አስፍሮታል ብለዋል።


መንገዶች ሁሉ በሁሉም አቅጣጫ የተዘጉበት የሰው በላው ስርአት ሃይሉን ከባህር ዳር በጀልባ ወደ ጎርጎራ እያመላለሰ መሆኑንም ጠቁመዋል።


ሊቦ ከምከም ወረዳ አዲስ ዘመን ከተማን በቁጥጥር ስር ያደረገው ህዝባዊ ሃይሉ አሁን ላይ መንገዶችን ሁሉ ዘግቶ ነጻንቱን አውጇል ሲሉም ተናግረዋል።


የምስራቅ ጎጃም ዞን ወረዳዎች እና ከተሞች የሆኑት አነቢቸና፣ ሸበል በረንታ፣ እናርጅ እናውጋ እና ሌሎቹም የሰው በላውን ሃይል በማስወገድ ነጻነታቸውን በማወጅ ላይ ናቸው ሲሉም ምንጮቹ አመልክተዋል።


ፍኖተሰላም ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ሆድአንሽና አካባቢው ላይ ከዚሁ ቡድን ጋር ሲታገል የነበረው ህዝባዊ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ የገዳዩን ሃይል በመደምሰስ ንጹህ አየሩን መተንፈስ ጀምሯል ብለዋል።


የዳንግላ የፖሊስ አዛዥም ምሽት ላይ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የሚናገሩት ምንጮቹ ህዝባዊ ሃይሉም በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚያደርገውን ትግል አፋጥኖታል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Comments


bottom of page