top of page

ሐምሌ 25/2015 በአማራ ክልል ባህርዳርና አካባቢው የኦህዴዱ ኦነግ ሃይል በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ጦርነት መክፈቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።




በአማራ ክልል ባህርዳርና አካባቢው የሚገኙ የፖሊስ ሃይል አባላትን መሳሪያ አስወርዶ በአንድ ላይ ያፈነው የኦህዴዱ ኦነግ ሃይል በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ጦርነት መክፈቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



ኢንተርኔትን በማቆራረጥ ጭምር በሁሉም አቅጣጫ ጦርነት የከፈተው ይሄው ስብስብ በደጋዳሞትም በንጹሃን ነዋሪዎች ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት መክፈቱን አመልክተዋል።



ዛሬ ቀን ላይ የተጀመረው ይሄ ጦርነት ህዝባዊ ፖሊሱን መሳሪያ በማስወረድና የፋኖ ህዝባዊ ሃይልን አጋዥ በማሳጣት መምታት በሚል እቅድ ነው ይላሉ።



ትላንት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ አቶ አደራው ጋሹ የአርበኛ ዘመነ ካሴን ክንፍ በሙሉ አጠፋለሁ በሚል ሲፎክር መዋሉንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።



ከዚህ ዛቻ በኋላም ዛሬ ገና ከረፋዱ በቀጥታ በተለያዩ አቅጣጫዎች የብአዴኑ ሆድ አደር ቡድን የኦህዴዱን ገዳይ ቡድን በመምራት የራሱን ወገን ማስገደሉን ቀጥሏል ብለዋል።



የአርበኛ ዘመነ ካሴ ሃይልን እመታለሁ ብሎ እየተንቀሳቀሰ ያለው ሃይል ደግሞ መቀመጫውን ያደረገው የአበባው ታደሰ የግል ንብረት በሆነው አልዋቅ ሆቴልና መኮድ አካባቢው መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

ወደ ፈረስቤት የገባው ገዳይ ቡድን ድኩል ካና ቀበሌ ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ወደ ንጹሃን የአማራ ተወላጆች ማስወንጨፉን መቀጠሉን ምንቾቹ ይናገራሉ።



ለሊቱን ከ10 ተሽከርካሪ በላይ የገዳይ ቡድኑን አባላት ወደ ደጋ ዳሞት ለማስገባት የሞከረው የሰው በላው ስርአት ስብስብ ገና ከመንገድ ላይ ጉዞው በፋኖ ህዝባዊ ሃይልና በህብረተሰቡ መገታቱን ይናገራሉ።



ወደ ጎጃም ደጋ ዳሞት በፈረስቤት እና በጥያሜ መካከል ድኩል ካና በሚባል ቦታ የገባው ይሄው ሃይል መውጫ አቶ በህዝባዊ ሃይሉና በህብረተሰቡ ተወጥሮ መያዙን ይናገራሉ።



ያንን ማሸነፍ ያልቻለው ስብስብም ከባድ መሳሪያዎችን በቀጥታ ወደ ንጹሃን መኖሪያ ማስወንጨፍ መቀጠሉ ነው የሚናገሩት።



ከብርሸለቆ ወደ ደጋዳሞት በመጣበት ፍጥነት ቢሆን ኖሮ አንድም የአካባቢው ነዋሪው አይተርፈውም ነበር ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ በፋኖና በህብረተሰቡ ኣጅ ላይ የገብ ኣው ይሄ የገዳዮች ስብስብ ሳይወድ በግዱ ሽንፈቱን እየተከናነበ ነው ሲሉ ምንጮቹ ሁኔታውን ገልጸዋል።



ደጋዳሞት ላይ የህዝባዊ ኃይሉን ምት መቋቋም ያቃተው የሰው በላው ስርአት ሃይል ከፍተኛ ቁጠ ያለው ሃይል ወደ ደምበጫ በማስገባት ጦርነት መክፈቱን አስታውቀዋል።



የደምበጫ ህዝብ እና የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ደግሞ ሊገላቸው ከመጣው ከዚህ ቡድን ጋር አንገት ለአንገት መተናነቃቸውን ገልጸዋል።



እስካሁንም ሁለት አርሶ አደሮች መቁሰላቸውንና ከገዳዩ ቡድንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይል ሙትና ቁስለኛ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


እየተዋደቀ ላለው የደንበጫ ህዝባን ፋኖ የአጎራባች ከተሞቹ የጅጋ፣የፍኖተሰላም፣የአማኑኤል፣የቋሪት እና መላው የአማራ ህዝብ ከደምበጫ ጎን እንዲሰለፉ አስቸኳይ ጥሪ ቀርቧል ብለዋል።


ሌላው ደግሞ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት ቡሬ ዳሞት ላይ የተከፋፈለው የገዳዩ ስርአት ሃይል እርስ በርሱ ጦርነት ውስጥ መግባቱንም የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።


በጎንደር ዙሪያውን ሰሞኑን በጦርነት ሲያምስ የከረመው ይሄው ስብስብ አሁን ደግሞ በአዘዞ የሚገኘውን ወታደራዊ ካምፕ በገዳዩ ቡድን ስብስብ ሞልቶታል ብለዋል።


ላስታ አውራጃ ላይ ደግሞ ለሰአታት ከገዳዩ ሃይል ጋር ጦርነት የገጠመው የፋኖ ህዝባዊ ሃይልና ህብረተሰቡ የላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያን በቁጥጥር ስር ማድረጉን ነው ምንጮቹ የተናገሩት።


ይሄን ሁሉ ጦርነት ደንበጫ ላይ የከፈተው የገዳዩ ቡድን 2 ፓትሮል ተሽከርካሪ ሙሉ ቀይ ቦኔትና 1 ፓትሮል የአማራ ልዩ ሀይል የለበሰ ስብስብ ከማርቆስ ተነስቶ ወደ አማኑኤል እያመራ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


አሁንም የጅጋ ህዝብ መንገድ ዘግቶ ካላስቀረው በስተቀር አምስት ኦራል ተሽከርካሪ ሙሉ የገዳይ ቡድኑ ሃይል ከብርሸለቆ ተነስቶ ወደ ደጋዳሞት እያመራ መሆኑንም ጠቁመዋል።


ከደብረማርቆስ እስከ ፍኖተ ሰላም ያለው መንገድ መዘጋቱን የሚገልጹት ምንጮቹ ገዳዩ አካል አሁንም ይሄው ስብስብ ወደ ደጋዳሞት ከባድ መሳሪያ ማስወንጨፉን ቀጥሎበታል ብለዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ የአማራ ህዝብ በዚህ መልኩ እየተገደለና እየተሳደደ ባለበት ሰአት ባለሃብቶች በምዕራብ ጎንደር በመተማ ወረዳ አልፋሽጋ ተብሎ በሚጠራውና ሱዳን በሃይል ወራ ከያዘችው መሬት ላይ ቦታ ለመግዛት ሽሚያ ላይ መሆናቸውን በአግራሞት ይገልጻሉ።


ኢትዮጵያ ባለመብት በሆነችበትና ቦታው ላይም ሲያለሙ የነበሩ ባለሃብቶች እንዲባረሩ በተደረጉበት ሁኔታ ውስጥ አሁን ከሱዳን ወታደሮች ጋር እየተደራደረ መሬት እየገዛ ያለው የትኛው ባለሃብት ነው የሚለው ጥያቄ ደግሞ ሌላውኛው ጉዳይ ነው ብለዋል ምንጮቹ።


በዚህ በግልጽ በታወጀ ጦርነት ውስጥ ደግሞ ሰው በላው ስብስብ አይን ባወጣ መልኩ በተሽከርካሪ ዝርፊያ ላይ መሰማራቱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ዝርፊያው ደግሞ መኪናውን ከነነፍሱ ከመውሰድ ጀምሮ ተሽከርካሪውን አራግፎ እስከመዝረፍ ይደርሳል ሲሉ የህግወጥነቱን ልክ አስምረውበታል።


የምዕራብና የምስራቅ ጎጃም ጎንደርና ወሎን ጨምሮ ዛሬ የጦርነት ቀጠና ሆነዋል የሚሉት ምንጮቹ በጅጋ ከተማና አካባቢው በገዳዩ ስርአትና በህዝባዊ ሃይሉ ፋኖ መካከል ከባድ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል።


ህብረተሰቡም ከፋኖ ህዝባዊ ሃይል ጎን በመቆም ገዳዩን ስርአት ፊት ለፊት መግጠሙን አመልክተዋል።


በከተማው አቅራቢያም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የገዳዩ ስብስብ ሙትና ቁስለኛ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በፍኖተ ሰላምና በጅጋ መካከል ሆዳንሽ ከተማ መግቢያ ላይ ደግሞ ገዳይ ቡድኑን ይዞ ይጓዝ የነበረ ኦራል ተሽከርካሪ በማህብረሰቡ ወደ አመድነት እንዲቀየረ ሆኗል ብለዋል።


ህብረተሰቡን ጨምሮ የፋኖ ህዝባዊ ሃይልም የማረከውን ብሬንና ስናይፐርን ጨምሮ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን መታጠቁንም ገልጸዋል።


በደንበጭና አካባቢው ገና በጠዋቱ በንጹሃን ላይ ጦርነት የከፈተው ገዳይ ቡድን የገጠመው ሃይል ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ወደ ኋላ ማፈግፈጉን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ይሄንን ያየውና ሆድ አደሩ የደንበጫ አስተዳደር የራሱን ህዝብ ከኋላ ከቦ ለማስመታት የአካባቢውን ሚሊሽና ፖሊስ ስብሰባ ጠርቶ መመሪያ እየሰጠ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ህብረተሰቡም ወደ ስብሰባው ቦታ በማምራት ይሄንን መመሪያ እየተቀበለ ያለ ሃይልን ማስቆም ካልቻለ ከባድ ጉዳት ሊፈጠር ይችላል ሲሉም ምንጮቹ ተናግረዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page