top of page

ሐምሌ 6/2015በሶማሊያ ሰላም አስከባሪ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከነመሳሪያቸው እየጠፉ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።




በሶማሊያ ሰላም አስከባሪ(አሚሶም)አባል የሆኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከነመሳሪያቸው እየጠፉ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


መሳሪያቸውን ይዘው የሚጠፉት የመከላከያ አባላቱ መሳሪያቸውን ይዘው ከወጡ በኋላም አየር ባየር እንደሚሸጡትም ይናገራሉ።


በአሚሶም ስር የሆኑት እነዚህ የሰራዊቱ አባላት መቀመጫቸው በለድወይኒ ከተማ ሲሆን ካለፈው ወር ጀምሮ ክላሻቸውን ለከተማ ሰው በ3ሺ ዶላር እየሸጡ በምጥፋት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ።


ከሸጡም በኋላ ወደ ተለያዩ ሃገራት እንደሚሸሹም አመልክተዋል።


በጣም የሚገርመው ወታደሮቹ ከመጥፋታቸው በፊት ወደ ከተማ ገብተው ልጠፋ ነው ክላሼን የሚገዛ ብለው ዋጋ ተደራድረው ሸጠው እዛው ላለ አሰኮብላይ ከሶማሊያ ኬንያ ከኬንያ ታንዛኒያ ከዛ ደቡብ አፍሪካ ድረሰ 1ሺ ዶላር ተሰማምተው እንደሚጠፉ ይናገራሉ


ትናንትናም የተፈጠረው ይላሉ ምንጮቹ አንድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እዛ ከተማ ለሚኖር ግለሰብ ከክላሸ ከፍ ያለ መሳሪያ ወይንም ሰናይፐር የሚባለውን በ3500 ሶሰት ሺህ አምሰት መቶ ዶላር ሸጦ መጥፋቱን ገልጸዋል።


ነገር ግን በዛ የተመደቡት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኮረኔሎች መሳሪያው በጣም ውድ በመሆኑና በዚያ ላይ እንደዛ አይነት መሳሪያ ከርቀት ማንንም ሰው መምታት ይችላል በሚል ከባድ ድንጋጤ ውስጥ መውደቃቸውን ይናገራሉ።


እናም ይላሉ ምንጮቹ በጭንቀት የተወጠሩት የጦር አመራሮቹ ከተማ ወደሚኖሩ ሸማግሌዎች አማላጅነት መሔዳቸውን አመልክተዋል።


በምልጃውም መሳሪያውን ለገዛው ልጅ ብሩን እንመልሰለታለን መሳሪያውን ብቻ ስጡን በሚል ሽማግሌዎቹን ሲያስጨንቁ መሰንበታቸውን ገልጸዋል።


በመጨረሻም ከስምምነት ላይ በመድረሳቸው ለልጁ ብሩን ከፍለው መሳሪያውን መውሰዳቸውን ተናግረዋል።


ከሁሉም የሚያሳዝነው ይላሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ስመ ገናናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በዚህ ደረጃ ክብሩ ወርዶ መታየቱ ነው ብለዋል።



Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page