top of page

ሐምሌ 6/2015የብአዴኑ ስብስብ ሰላም አስከባሪ ሃይል በሚል አዳዲስ አባላት እየመለመለ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



የብአዴኑ ስብስብ ሰላም አስከባሪ ሃይል በሚል አዳዲስ አባላት እየመለመለ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


ስብስቡ የአማራ ልዩ ሃይልን ከበተነ በኋላ የክልል ፖሊስ በሚል አዲስ ሃይል አሰልጥኖ እንደነበር ይናገራሉ።


ነገር ግን ካሰለጠኑት ሃይል አብዛኛው ከነመሳሪያ ሲከዳ የተቀረውም ቢሆን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ሲሉም የሆነውን ይናገራሉ።


አሁን ደግሞ ከፋኖ ህዝባዊ ሃይል ጋር ይዋጋልናል ብሎ ያሰበውን ስብስብ ሰላም አስከባሪ በሚል እያደራጀ መሆኑን ያነሳሉ።


ትላንትም በፍኖተ ሰላም ኪዳነምህረት ሰፈር አካባቢ የፋኖ ህዝባዊ ሃይልን እከባለሁ ብሎ የነበረው የዚሁ ፍንካች የሆነውና የብአዴን ጥምር ጦር በሚል የዳቦ ስም የተሰጠው አካል ነው ይላሉ።


ነገር ግን ከበባውም ሆነ ስምሪቱ ሰአትን ባልወሰደ ሁኔታ ውስጥ እንዲከሽፍ ሆኗል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


በተለያየ መንገድ ወጣቱን እያባበለ የተለያየ አደረጃጀት ውስጥ ለማስገባት መከራውን እያየ ያለው የሆዳሞቹ ስብስብ በሁሉም አቅጣጫ አደራጀሁት የሚለው ሃይል አንድ ጥይት እንኳን በወገኑ ላይ ሳይተኩስ ከነመሳሪያው መሰወሩ ትልቅ ራስ ምታት ሆኖበታል ብለዋል።

አዲስ እያቋቋምኩት ነው የሚለው የሰላም አስከባሪ ሐይልም አስቸኳይ ስልጠና እንዲወስድ ትእዛዝ መተላለፉንም ይናገራሉ።


ወደ ሌሎች አካባቢዎች እስኪዳረስም ለጊዜው ስልጠናው በሞጣ፣በሉማሜና በአማኑኤል እንዲሰጥ መወሰኑንም ገልጸዋል።


በአንድ ቦታ እንዲሰለጥን የተመለመለው ሃይል ከ150 በላይ መሆኑንና ለእያንዳንዱ ሰልጣኝ ቀለብ እንዲሰፍሩ ደግሞ በአካባቢው ላሉ ሆቴሎች ትእዛዝ መተላለፉን አስታውቀዋል።


ነገር ግን የሆድ አደሩ ስብስብ ሃይል አሰለጥናለሁ በሚል የተነሳበት አካሄው ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ ከራሱ ከሰልጣኙም ሆነ ከህብረተሰቡ ከባድ ተቃውሞ ገጥሞታል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።


አሁንም ኦህዴድን ለማስደሰት ህዝብን እያስጨረሰ ያለው የብአዴኑ የላይኛው አመራር ደግሞ የስርአቱ መፍረሻ መድረሱን በመረዳቱ ቤተሰቡን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቤተሰቡን በማሸሽ ላይ ነው ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page