በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከ23 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጅ የህክምና ባለሙያዎች መታፈናቸውንና እስካሁንም ያሉበት አለመታወቁን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
አስቀድሞ የህክምና ባለሙያዎችን ሲሰልልና ሲያሰልል የቆየው አካል በስተመጨረሻ አማራ የሆኑት ብቻ ተመርጠው መታፈናቸውን ይናገራሉ።
አብዛኞቹ የህክምና ባለሙያዎች የታፈኑት ስራ ላይ ባሉበት ሰአት ሲሆን ሌሎች ባለሙያዎች ደግሞ ከየቤታቸውና ከየተገኙበት አካባቢው መታፈናቸውን ነው የሚናገሩት።
እስካሁንም በዚሁ ቡድን ከታፈኑትና ያሉበት ቦታ ካልታወቀው መካከልም ዶ/ር ዮናስ፣ ዶ/ር ስመኘው፣የነርሶች ሀላፊ የሆነው አትርሳው፣ነርስ ልጃዲስ፣ ፋርማሲስቱ ትንሳኤ፣ የህፃናት ድንገተኛ ክፍል ሀላፊ ስለሺ፣ የድንገተኛ ማዋለጃ ክፍል ሀላፊ አሰፋና ሌሎችም እንደሚገኙበት ይናገራሉ።
ኣነዚህ የህክምና ባለሙያዎች በሆስፒታሉ ውስጥ አሉ የሚባሉና ለህሙማኑ ጥሩ አገልግሎት ይሰጣሉ የሚባሉ ሲሆን ነገር ግን አማራ በመሆናቸው ብቻ በዚህ ሰው በላ ቡድን ታፍነው ተወስደዋል ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል።
ቤተሰቦቻቸውና የሙያ አጋሮቻቸው ያሉበት ቦታ ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን ግን ያሉበትን ቦታ ማግኘት አለመቻላቸውን ነው የሚናገሩት።
Comments