በጎጃም ደብረማርቆስ ያለውን የገዳዩን ቡድን ምሽግ የተቆጣጠረው ህዝባዊ ሃይሉ አባዛኛውን አካባቢዎ ነጻ እያወጣ መሆኑን የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ዛሬ መርጦ ለማርያምና ሞጣ ላይ ህዝባዊ ሃይሉ ውጊያ ላይ ነው የሚሉት የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ማርቆስ ላይም በተወሰነ ደረጃ ውጊያ መኖሩን ይናገራሉ።
አካባቢውን ለቆ የወጣው ገዳይ ቡድን ግን ወደ ሽምቅ ውጊያ ገብቷል ሲሉ ያለውን እውነታ ይናገራሉ።
ገዳይ ቡድኑ የአማራ ህዝባዊ ሃይልን በምንም መልኩ ማሸነፍ እንደማይችል ማወቁን ተከትሎ ውጊያውን ወደ ሽምቅ ሊያዞር መሆኑን ኢትዮ 360 አስቀድሞ በመረጃው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ቡሬና ፍኖተ ሰላምን ነጻ ያደረገው ህዝባዊ ሃይሉ አማኑኤልንም ሙሉ በሙሉ ነጻ አድርጎና የገዳዩን ቡድን ምሽግ ሰብሮ አካባቢውን ተቆጣጥሯል ብለዋል።
ኢንተርኔት አቋረጦ ህዝባዊ ሃይሉን አመታለሁ ብሎ ያሰበው ገዳይ ቡድን ትልቅ ነው የሚባለውንና መሽጎበት የነበረውን የኮሶበር ማዘዣ ጣቢያውንም በራሱ ጊዜ ለቆ እንዲሄድ ሆኗል ትላንት ምሽትም ህዝባዊ ሃይሉ ተቆጣጥሮታል ብለዋል።
ከባህርዳር ተነስቶ መራዊ እገባለሁ ብሎ ያሰበው ሃይልም መራዊ ላይ እንዲመለስ ሆኗል የሚሉት የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ከደንበጫና ከደብረማርቆስ ውጪ ሌላው አካባቢ ነጻ ነው ሲሉ ይናገራሉ።
ደጀን፣ሞጣና ባህርዳር ላይ ያለው ሁኔታም ቢሆን ብቸና ላይ በተወሰነ ደረጃ የሚንቀሳቀሰው ገዳይ ቡድን በሽምቅ ህዝባዊ ሃይሉን ለመውጋት እየሞከረ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።