በደቡብ ክልል የኮሬ ማህበረሰብ ይኖርበት ከነበረው የነጭ ሳር አካባቢው በግዴታ እንዲፈናቀል እየተደረገ መሆኑን ተወላጆቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ማህበረተሰቡ እየተፈናቀለ ያለው በአካባቢው እንዳይኖር ለማድረግ ብቻ ሳይሆን የብሔር ማንነቱ ተለይቶ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።
የሰው በላው ስብስብ ከኖረበት ቀየው እንዲፈናቀል እየተደረገ ባለው የኮሬ ህዝብ ላይ ግልጽ ዘመቻ ተከፍቶበታል ብለዋል።
የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ሲመሰረት ዋና መስራቹ የኮሬ ህዝብ ነበር የሚሉት ተወላጆቹ ዛሬ ላይ ብሔሩ ብቻ ምክንያት ሆኖ የበቀል እርምጃ እየተወሰደበት ነው ሲሉ በመረጃቸው ላይ አስቀምጠዋል።
ከአካባቢው እንዲፈናቀል የተደረገው ይሄ ማህበረሰብ በግዴታ ወደ ማይፈልግበት አካባቢው እንዲወሰድ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።
በአካባቢው በስካውትነት የሚያገለግሉ 2 የጋሞና 7 የአማሮ ተወላጆችም በግዳጅ ወደማይመለከታቸው አካባቢው ተወስደዋልና በአስቸኳይ ወደ ነበሩበት ሊመለሱ ይገባል ሲሉም ይጠይቃሉ።
የኮሬ ህዝብ የፓርኩ መሥራች ሆኖ እያለ ዛሬ በጉልበተኞች ባዳ ሆኗል የሚሉት ተወላጆቹ በተለይም በጎማይዴ አካባቢ ከነበረው ችግር ጋር አገናኝቶ የኮሬን ህዝብ ማጥቃት ተገቢ አይደለም ብለዋል።
የኮሬ ህዝብ ታሪካዊ መረጃዎችን ለማውጣት ይገደዳል የሚሉት የአካባቢው ተወላጆች ነጭ ሳርን በጉልበት ለመንጠቅ የታሰበውን ነገር ለማስፈጸም ካልሆነ በቀር ፓርኩ የኮሬ ማህብረሰብ ስለምሆኑ በማስረጃ ጭምር ማሳየት ይቻላል ሲሉ በመረጃቸው አመልክተዋል።
አሁንም ይሄንን እያደረገ ያለው አካል ከድርጊቱ ሊቆጠብ ይገባል፣የሚመለከተውም አካል የሚሰራውን አይን ያወጣ ወንጀል ሊያስቀም ይገባል ሲሉ ተወላጆቹ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።