ከከሚሴ የገባው ገዳይ ቡድን ጭራ ሜዳ ላይ ከነሙሉ ሰራዊቱ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን መደረጉን ይናገራሉ።
ሰላ ድንጋይን ነጻ ያወጣው ሃዝባዊ ሃይልን እየሸሸው ያለው ገዳይ ቡድኑ ብቻ ሳይሆን ሆድ አደሩ የብአዴን ቡድን መሆኑ ነው የሚናገሩት።
የተከበበው ሃይሉን ለማስለቀቅ የገባው ገዳይ ቡድን ጣርማ በር ላይ ከባድ ውጥረት ላይ ገብቷል ብለዋል።
አንኮበር ላይ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የሚናገሩት የህዝባዊ ሃይሉ አባላት በዚህ ጦርነት ደግሞ የአፋር ሃይል ከአማራ ወገኑ ጎን ተሰልፎ እንደነበርም ገልጸዋል።
በአካባቢው የወደቀውን አስከሬኑን መሰብሰብ ያልቻለው ገዳይ ቡድን ወደ ከተማ ለመግባት ቢሞክርም መረጋጋት ግን አልቻለም ብለዋል።
ዘርቃሚ ላይም ጦርነት የከፈተው ገዳይ ቡን በሚገባው መልኩ ዋጋውን አግኝቷል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ከበባው ውስጥ የገባው ገዳይ ቡድን ያፈናቸውን የከተማዋን አንቂዎች፣የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችን ወደ ሌላ አካባቢው ለመውሰድ ያደረገ ጥረትም በህብረተሰቡ ትግል ሊሳካለት አልቻለም ሲሉ ገልጸዋል።
ወደ ድምድምና በቆላማው አካባቢ የነበርው ገዳይ ቡድን በቆረጣ ተከታታይ ጥቃት እንደተፈጸመበትም ይናገራሉ።
ይሄንን ሽንፈት መቀበል ያልቻለው ገዳይ ቡድን ከባድ መሳሪያውን ወደ አገኘው አቅጣጫ እየተኮሰ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
የወንጭት ተፋሰስን ይዘው የመጡ የዚሁ ሃይል አባላት ደግሞ ህዝባዊ ሃይሉን መቀላቀላቸውን ነው የሚናገሩት
መንዲዳ ላይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር አድርጎ የቆየው ገዳይ ቡድን ነቅሎ ወደ አዲስ አበባ እየሸሸ መሆኑን ነው የሚናገሩት።
ህዝባዊ ሃይሉ በዚህ መልኩ ትግል ሲያደርግ የሆድ አደሩ ስብስብ ደግሞ ንጹሃንን በማሳሰርና በመጠቆም ስራ ላይ ተሰማርቷል ብለዋል።
እነዚህ ደግሞ በቃችሁ ሊባሉ ይገባል ሲሉም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።