top of page

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ።


በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱንና መሳሪያቸውን ሙሉ በሙሉ መማረኩን አባላቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።


ህዝባዊ ሃይሉ በጥምር ጎንደር ላይ ዘመቻ በወሰደበት ወቅት ወደ ጭንጫዬ የገባ ገዳይ ቡድን ንጹሃን የአማራ አርሶ አደሮችን ከየቤታቸውን እያወጣ በአደባባይ እንደረሸናቸው ይናገራሉ።


ይሄን የሰሙት የሰሙት የህዝባዊ ሃይሉ አባላትም በቀጥታ ወገኖቻቸው በግፍ ወደ ተገደሉበትና አስከሬናቸው እንኳን ተነስቶ የቀብር ስነስርአታቸው እንዳይፈጸም ወደ ከለከለው ጨካኝ ቡድን መሆኑን ይናገራሉ።


የወገኖቻቸውን አስከሬን በክብር እንዲያርፍ ካደርጉ በሁላ ግን በቀጥታ ያመሩት ገዳይ ቡድኑ ያለበትን አካባቢ ወደ ማጥናት መሆኑንም ገልጸዋል።


ሁሉንም መረጃ አሰባስበው ከጨረሱ በኋላም ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ላይ በቀጥታ ሄደው ገዳይ ቡድን ላይ ውጤታማ የሆነ እርምጃ መውሰዳቸውን ይናገራሉ።


በየፖሊስ ጣቢያውና በኮሌጅ ውስጥም በግፍ የታፈኑትን ሁሉ ማስፈታታቸውን የሚናገሩት የህዝባዊ ሃይል አባላቱ ሶስት ወገኖቻቸው ቢሰውም፣የተወሰኑት ቢቆስሉም ወደ ኋላ የቀረ አንድ አባላቸውን ቆራርጠው ቢገሉባቸውም እነሱ ግን ከፍተኛውን ድል ተቀዳጅተው መውጣታቸውን ነው አስታውቀዋል።

በዚህ ዘመቻ አራት ብሬል፣40 ክላሽ፣አንድ ስናይፐርና የማይሰሩ 20 ክላሶችን ማርከው መውጣታቸውን ይናገራሉ።


የጭንቻዬ ንጹሃን አርሶ አደሮችን በግፍ የገደለው ሰው በላ ቡድን ዛሬም በአካባቢው የነበረ አንድ የገጠር ቀበሌ ሊቀመንበርን መረሸኑንም ነው ለኢትዮ 360 የገለጹት።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እነጎበዜ ሲሳይንና ሌሎቹን የሚሰልል ሰው መመደቡን የኢትዮ 360 ምንጮች ተገለጹ።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት 6ኛ የታሰሩት እነ ጎበዚ ሲሳይ ጋ ወርቁ ደምሴ የሚባል በጣም አደገኛና በማረሚያ ቤቱ የቆየ እስረኛ ወደ እነሱ ክፍል እንዲዛወር መደረጉን አስታውቀዋል። ይሄ ግለሰብ ከዚህ በፊት በርካታ ሰዎችን...

Comentários


bottom of page