በተቋሙ ውስጥ ያሉ ከላይ ካለው አመራር ጀምሮ እስከ ታችኛው እርከን ያለውን አመራር በዚሁ ሌብነት ውስጥ ተሳታፊ መሆኑን ይናገራሉ።
የአውሮፕላን መፍቻ እቃዎች፣የተሽከርካሪ ቸርኬዎች፣ለአውሮፕላን ጥገና አገልግሎት የሚሉ ንብረቶች ሁሉ እየተዘረፉ መሆኑን ነው የሚናገሩት።
ከአየር ሃይሉ ጋር ቁርኝት ያላቸው ባለሃብቶችም በተቋሙ ስም የሚለምኑትን ሃብት በሙሉ ለራሳቸው ጥቅም ኣያኣሉት መሆኑን አጋልጠዋል።
በተቋሙ ይሄ ሁሉ ሌብነት እየተፈጸመና በውስጥ የሚሰራው ወንጀል አይን ባወጣበት ሁኔታ ሰሞኑን እነ ይልማ መርዳሳ "የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በመሻገር በታላቅ ሀገር ታላቅ አየር ኃይል እንገነባለን" በሚል ሰራተኛውን ለማወያየት መጥራታቸውን ይናገራሉ።
ይሄ ርዕስ ተይዞ ወደ ውይይት ይገባ እንጂ ሰራተኛው ግን አንድ ሳምንት ሙሉ ምን ለማለት እንደፈለጉ ሳይገባው ውይይቱ አልቋል ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።
ነገር ግን ይላሉ ርዕስ ተሰቶት እንወያይ ተብሎ የተመጣበት መንገድ ግን አንድም ሰራተኛውን የመደናበር ሌላም አራዳ መስለው በመቅረብ በጅምላ ለማሰር ምክንያት ስላጡ በተናጠል ሰራተኛውን እናገኛለን ብለው አስበው ነው ሲሉ የውይይቱን ዋና አላማ ያስቀምጣሉ።
ከአማራ አካባቢ የመጣውን የሰራዊት አባል ለማበሳጨት ደግሞ ፅንፈኛ ፋኖ:ዘራፊው ፋኖ: የመሳሰሉ ቃላቶችን ሲጠቀሙ መክረማቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ከዚህም ሌላ በተከታታይ በኢትዮ 360 የወጡት ሚስጥራዊ መረጃዎች ያስደነገጠው ይሄው ስብስብ ከተቋሙ መረጃ ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ አለ የሚለው አጀንዳም በመድረኩ የተነሳ ዋነኛ ጉዳይ ነበር ብለዋል።
የውይይቱ መሪዎች ሀገራዊ ሚዲያ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እያለ የጠላት ሚዲያ የሚከታተል አለ የምታውቁ ካላችሁ እከሌ በሉና ተስተካክሎ ከስተቱ እንዲታረም እናድርገው የሚል የሞኝ ጥያቄም እንደተነሳ ገልጸዋል።
በተቋሙ ህግ መሰረት አንድ አብራሪ የጀነራልነት ማዕረግ ካገኘ መብረር እንደማይቻል እየታወቀ ይልማ መርዳሳ ኮ/ል ብሩክን በቻ በመያዝ የተቋሙን ደንብ በመተላለፍ በማናለብኝነት የበረራ ስልጠናቸውን በመስጠት ላይ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በዚህ ስልጠና ውስጥ ደግሞ ለነሱ ያደረ ባንዳ ካልተጠራ በቀር ሙሉ በሙሉ በስልጠናው ላይ እንዲሳተፍ የተደረገው የባለጊዜው ስብስብ ብቻ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።