በደብረታቦር እስር ቤት እየተንገላቱ የሚገኙት የአማራ ልዩ ሃይል አሰልጣኞች ፍርድ ቤት ነጻ እንዲወጡ ትእዛዝ ቢሰጥም የፖሊስ መምሪያው ግን እንዳይወጡ መከልከሉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በነሃሴ 29/2015 ነጻ ተብለው የተሳነበቱት የልዩ ሃይል አሰልጣኞች በፖሊስ መመሪያው ሃላፊ ኮሚሽነር አየልኝ ትእዛዝ ሰጭነት እንይፈቱ መደረጉን ተናግረዋል።
ነገር ግን ታራሚዎቹ ለምን አንፈታም በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ኮማንድ ፖስቱ ነው እንዳትፈቱ ያዘዘው የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውም ይናገራሉ።
ስለጉዳዩ የተጠየቀው ኮማንድ ፖስት ግን በዚህኛው ኮማንድ ፖስት ጊዜ የታሰሩ ስላልሆኑ እኛ አንፈልጋቸውም በሚል ቁርጥ ያለ ምላሽ መስጠቱንም አስታውቀዋል።
ይሄንን ሁሉ ምክንያት እየፈጠሩና እነዚህ ወጣቶች እንዳይፈቱ እያደረጉ ያሉት የብአዴን ሆድ አደር ስብስቦች አሰልጣኞቹ ቢፈቱ ለህዝባዊ ትግሉ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋሉ የሚል ስጋት ስላደርባቸው ብቻ ነው ሲሉ ሁኔታውን አስቀምጠዋል።
አሁን ላይ ወጣቶቹ እየተንገላቱና በእስር እየማቀቁ ያሉት ምንም ጥፋት ኖሮባቸው ሳይሆን የግለሰቦች የግል እስረኛ በመሆናቸ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።