በሰሜን ሸዋ አሳግርትና አካባቢው የገዳዩ ቡድን ከባድ መሳሪያዎችን ወደ ንጹሃን መኖሪያ እያስወነጨፈ መሆኑን የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ህዝባዊ ሃይሉን ማግኘት ያልቻለው ገዳይ ቡድን ትላንት ሃሙስ ገበያ ላይ የጀመረውን ጦርነት ወደ አሳግርት አካባቢ ለማምጣት እየሞከረ ነው ይላሉ።
አካባቢውን ከህዝባዊ ሃይሉ መንጠቅና ህዝባኢ ሃይሉን ማግኘት ያልቻለው ይሄው ቡድን ወደ ንጹሃን ዜጎች ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው ብለዋል።
የጫጫ አካል በሆነችው አሳ ባህር ላይ ሆኖ ነው አሁን ጦርነቱን የከፈተው ብለዋል።
ሌላው ትኩረት መደረግ ያለበት ይላሉ የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ሚዳ ላይ ያለው ጉዳይ ነው ይላሉ።
ህዝባዊ ሃይሉ ንጹሃንን ላለማስመታት ከተዋን ለቆ ሲወጣ ወደ አካባቢው የገባው ገዳይ ቡድን ህብረተሰቡን ሰብስቦ ለማወያየት መሞከሩን ይናገራሉ።
ነፍጥ ተሸካሚ በሚል የሚታወቀው የሚዳ ህዝብ ወደ ሬማና አለም ከተማ የሚያደርገውን ጉዞ እንዲያግዘው ጥያቄ ማቅረቡን ገልጸዋል።
ተሰብሳቢው ግን መከላከያ ሃገርን ሲጠብቅና ድንበር ሲያስከብር እንጂ መንደር ለመንደር የሚልከሰከስ አይደለም ሲሉ ነዋሪዎቹ በግልጽ እንዳስቀመጡላቸው ተናገረዋል።
የፋኖ ስምን ለማጠልሸት የተነሳው ሃሳብም ቢሆን ከእውነት የራቀና የፋኖ ማንነት እነሱ ከገለጹት በእጅጉ የተለየ መሆኑን በግልጽ እንደነግሯቸው አንስተዋል።
ነገር ግን ይሄንን ስብሰባ ሲመሩ የነበሩት የገዳዩ ብዱን ስብስብ ግን ይሄንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ከልጆቻቸው ጋር እንዲዋጉ እንደሚደረጉ እንደተነገራቸው ነው ያስቀመጡት።
የአካባቢው ማህበረሰብ እየተሰራ ያለውን ተንኮል አውቆ ልጆቹ ላይ ምላጭ መሳብ እንደሌለበት ማወቅ አለበት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
እስካሁን ምንም አይነት ለውጥ አልታየም የሚሉት የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ይሄንን ሳይሰማ ለገዳዩ ብዱን እወግናለሁ የሚል ካለ ግን ርምጃው የሚጀምረው ከራሱ ይሆናል ሱሉም ተናግረዋል።
ከዚህ በላይ ግን በደንብ ሊነገረው የሚገባና ከገዳዩ ቡድን በላይ ለአማራው ጠላት እየሆነ ያለው አርፋ ብተና ነው ብለዋል።
ትላንት ዲሽቃ ተሰቶት ዛሬ ጦርነት በወገኑ ላይ የከፈተው ይሄው ሆድ አደር ቡድን የማያርፍ ከሆነም ርምጃው የሚጀመረው ከራሱ ይሆናል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
በምንጃር አካባቢ ያለውን ሁኔታ እጅግ አስደሳች ነው የሚሉት የህዝባዊ ሃይሉ አባላት በአዲስ አበባ ዙሪያ ምሽግ እየቆፈረ ያለው ገምሹ ኮንስትራክሽን የሚባል የገዳዩ ቡድን ተባባሪ ነው ብለዋል።
ባለፉት አመታት የአማራ በመጀትን በመብላት ጭምር መንገዶችን አበላሽቶ የተቀመጠው ይሄው ተቋራጭ ዛሬ ደግሞ አማራውን ለማስጨረስ ምሽግ ቁፋሮ ላይ ነው ያለው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
Comments