በአዲስ አበባ በተለምዶ ሽሮ ሜዳ የሚባለው አካባቢ ማህበረሰቡ የእግረኛ መንገድ በማጣቱ ለከፍተኛ የትራፊ አደጋ መጋለጡን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ይሄ ችግር ሊፈጠር የቻለው ደግሞ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ አምባ በቀድሞ ስሙ አማሃ ደስታ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት የሆኑት የባህል ልብስ መሸጫዎች በኦህዴዱ ስርአት መዘጋታቸውን ተከትሎ ነው ይላሉ።
መደብሮቹን ከዘጋ በኋላ አካባቢውን በገመድ ያጠረውና በመሳሪያ እያስጠበቀው ያለው ስርአት ነዋሪውን መንቀሳቀሻ አሳጥቶታል ብለዋል።
በሱቆቹ አጠገብ ለእግረኛ ተብሎ የተሰራው መንገድ በሙሉ በዚሁ አካል ዝግ እንዲሆን መደረጉን ነው ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ ያሰፈሩት።
መራመጃ ያጣው የአካባቢው ነዋሪም ለተሽከርካሪ የተሰራውን መንገድ ለመጠቀም ተገዷል ብለዋል።
ይሄ ደግሞ ማህበረሰቡን ለከፋ የትራፊክ አደጋ እያጋለጠው ነው ሲሉም የተደቀነውን አደጋ አስቀምጠዋል።
ነዋሪዎቹ የመኪና አዳጋ ተፈጥሮ የሰው ህይወት ከመንጠቁ በፊት ህብረተሰቡ እራሱን እንዲጠብቅና ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ደግሞ በአፋጣኝ መፍትሄ ይስጠን ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው አፈሳ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
በተለይ በየሰፈሩና አካባቢው ግንባር ቀደም ናቸው የሚባሉና በህበረሰቡ ውስጥ ተሰሚነት አላቸው የሚባሉ ወጣቶችን ሁሉ በየቤታቸው እየታደኑ መሆኑን ይናገራሉ።
በተለይ ሰሞኑን ከመስኪድ ፈረሳ ጋር በተያይዘ ከሙስሊም ወንድሞቻቸው ጎን የቆሙ ወጣቶች በሙሉ እየታደኑ መሆኑንም ገልጸዋል።
ከገዛ ቀየውና ከየመኖሪያ ቤቱ እየታፈሰ ያለው ወጣት በዚሁ ገዳይ ቡድን መያዙን እንጂ ወዴት እንደሚወሰድም የሚታወቅ ነገር ለመኖሩን ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የተናገሩት።
Comments