ሰኔ 1/2015ብሔረ ብጹአን መልካ ስላሴ ገዳም በህይወት የተገኙት 200 ያህሉ ብቻ መሆኑን ምእመናኑ ገለጹ።
- Ethio 360 Media 2
- Jun 8, 2023
- 1 min read
ብሔረ ብጹአን መልካ ስላሴ ገዳም የኦህዴዱ ሃይል ከፈጸመው ጥቃት ጋር ተያይዞ እስካሁን በገዳሙ ውስጥ ከነበሩት ከ600 በላይ መነኮሳት በህይወት የተገኙት 200 ያህሉ ብቻ መሆኑን ምእመናኑ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
በገዳሙ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር ተያይዞ የደረሰውን ጉዳት መናገር ከባድ ነው ይላሉ።
በገዳሙ አራት አብያተ ክርስቲያናት አሉ በሁሉም ላይ ጉዳት ደርሷል፣ለጸበልተኞች የተዘጋጀው ቦታና የመነኮሳት ምግብ ማዘጋጃ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፣የደረሰውን ጉዳት በዋጋ መተመን እንኳን አይቻልም ብለዋል።
በዚሁ ቡድን ከተፈጸመው ጥቃት ጋር ተያይዞ በገዳሙ የነበሩ ወደ ሰማንያ ከሚሆኑት የአብነት ተማሪ ህጻናት በህወት ተርፈው የተገኙት ሶስት ብቻ ናቸው ሲሉ የተፈጸመውን ወንጀል ይናገራሉ።
በዚሁ ጥቃት ምን ያህል መነኩሴ ተገደለ የሚባለውን ማወቅ ባይቻልም በዚሁ ሃይል በግፍ የተጨፈጨፉት ግን በቁጥር ከፍተኛ መሆናቸውን አመልክተዋል።
በገዳሙ ውስጥ የነበሩት መነኮሳት ቁጥር ከ600 በላይ ቢሆንም አሁን ላይ በህይወት ሊያገኙ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑትን ብቻ ነው ብለዋል።
በገዳሙ ውስጥ ተረፉ የተባሉትን እናቶች ገብቶ እንኳን ማዳን አልተቻለም ይላሉ።
ከ300 በላይ የገዳሙ ከብቶች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ይኑሩ አይኑሩ እሱንም ለማወቅ ወደ ገዳሙ መግባት ለተቻለም ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።