በአፋር ክልል በትምህርት በጤና ፣ በመልሶ ግንባታ መዋል የነበረበት የአፋር ዓመታዊ በጄትም ሆነ ለክልሉ የተደረጉ ድጋፎች በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እየተመዘበረ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
የክልሉ ካቢኒ አመራር በሙሉ በሚባል ደረጃ በህግ የተፈቀደለት እስኪመስል ድረስ የራሱን ቪላ ቤቶች ከመገንባት ጀምሮ ለሽርሽር የሚሆነው ገንዘብ የሚመደበው ከክልሉ በጀት ነው ያላሉ።
ይሄ ደግሞ የክልሉን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን የማደግና የማልማት እድል ወደ ዜሮ እንዲመለስ አድርጎታል ብለዋል።
በተለይ የአመራሩ በሌብነት መዘፈቅ ብቻ ሳይሆን በቤተዘመዳ በጎሳ የተተበተበ መሆኑ ደግሞ የሌብነቱን አካሄድ ውስብስ አድርጎታል ይላሉ።
ከክልሉ ፕሬዝዳንት አወል አርባ ጀምሮ እስከ ታችኛው አመራር ድረስ በቤተዘመድና በጎሳ የተሞላው የክልሉ አስተዳደር ለከፋ ረሃብና ድህነት የተጋለጠውን የአፋር ህዝብ ተመልካች እንዲያጣ አድርጎታል ብለዋል።
በሌብነት በተዘፈቀው አስተዳደር የሚመራ ህዝብ ረሃብና ችግርን መቋቋም አቅቶት የሞት አፋፍ ላይ ባለበት በዚህ ሰአት እንኳን አንድም አካል ደርሶ ሊታደገው ፍላጎቱም ቀናነቱም የለም ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
አነዚህ አመራሮች አማካኝነት በሚሊየን የሚቆጠረው ህዝብ ኋላቀር እንዲባልና በሌላው አካል ትኩረት እንዳያገኝም አድርጎታል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
Comments