top of page

ሰኔ 1/2015 በጅንካ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ሰብሳቢ ቀጀላ መርዳሳ ትእዛዝ ስልጣን እየተሰጠ መሆኑን ገለጹ



በጅንካ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ሰብሳቢ ቀጀላ መርዳሳ ትእዛዝ ሰጭነት ብቻ በዩኒርስቲው ለኦህዴዱ ያግዛሉ ለሚባሉ ሰዎች ስልጣን እየተሰጠ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



በተለይ የኦሮምኛ ቋንቋ ይችላሉ የሚባሉ የኮንሶ አካባቢው ተወላጆች በዚህ ሹመት ዋና ተመራጭ መሆናቸውን ይናገራሉ።



በዩኒቨርስቲው ህግ መሰረት አንድ ሹመት ሲሰጥ የቦታውን መስፈርት ከማሟላት ጀምሮ የተለያዩ ደረጃዎችን በማለፍ መሆኑን አመልክተዋል።



ነገር ግን አሁን በቀጀላ መርዳሳ እየተሾሙ ያሉት ሰዎች ይሄን ደረጃ ማለፍ አይደለም በዩኒቨርስቲው ውስጥ ለጠፋው በሚሊየን ለሚቆጠር ገንዘብ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሆኑ ሰዎች መሆናቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።



በዩኒቨርስቲው ለጠፋው ከአርባ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ማብራሪ እንዲሰጥ ጥያቄ እየቀረበና ከዚህ ጋር ተያይዞ የተመሰረተ ክስ እንዳለ እየታወቀ በቀጀላ መርዳሳ ትእዛዝ ሰጭነት በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎች እየተሾሙ ነው ብለዋል ምንጮቹ።



ከነዚህ መካከል ደግሞ የአስተዳደር ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ዶክተር አለሙ አይላቴና የአካዳሚክ፣የምርምር፣የቴክኖሎጂ፣የሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳትን ሆነው የተመደቡት ዶክተር ኤልያስ አለሙ እንደሚገኙበት ምንጮቹ ተናግረዋል።


በዩኒቨርስቲው ያለው አሰራር በሌብነትና በዘረኝነት የተሞላ ሆኖ ሳለ አሁን ደግሞ በቀጀላ መርዳሳ እየተሰራ ያለው ህገወጥ አሰራር ዩኒቨርስቲውን የበለጠ እየገደለው ነው ብለዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page