ሰኔ 22/2015በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ከአራት በላይ የትምህርት ክፍሎች እንዲዘጉ መደረጋቸውን አስታወቁ።
- Ethio 360 Media 2
- Jun 29, 2023
- 1 min read
በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ትምህርት ክፍል ብቻ ሳይሆን ከአራት በላይ የትምህርት ክፍሎች እንዲዘጉ መደረጋቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ከአማርኛ ትምህርት ክፍል ውጪ የታሪክ፣የዜግነት፣የፊዚክስም፣የማህበራዊ ሳይንስና ሌሎች የትምህርት ክፍሎች እንዲዘጉ መደረጋቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።
እነዚህ ሁሉ የትምሀር ክፍሎች እንዲዘጉ የተደረገው ደግሞ በዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ንጉሱ ታደሰ ትእዛዝ ሰጭነት መሆኑን አስምረውበታል።
ሌሎች ተጨማሪ ክፍሎችን ለመዝጋት ዝግጅት መኖሩንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በስሩ ያሉ ዳይሬክቶሬቶችን ውድድር ከልክሎ በራሱ ደብዳቤ የሚመድበው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት የአካባቢ ታሪክ ፣ የአካባቢ ቋንቋና ትውፊት፣ የስራ እድል የምትሉት ነገር አይመለከተኝም በሚል ሰራተኛውን ማሰቃየቱን ቀጥሎበታል ይላሉ።
እኔ የፌደራል መንግስት ተወካይ ነኝ የምሰራውም ለዚያ መርህ ነው በሚል በግልጽ የሚናገረው ፕሬዝዳንት ዩኒቨርስቲውን ከህግና ከስርአት ውጪ አድርጎ ሊያዘጋው ከጫፍ ደርሷል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንቾች ገልጸዋል::