አሁን ላይ ሁሉም የብአዴን ሹመኞች እና ሚዲያወቻቸው ስለልምትና መሰል ጉዳዮችን ብቻ እንዲናገሩ፥ እንዲጽፉ በመወረደላቸው መመሪያ መሰረት ተግባራዊ እያደረጉት ነው ይላሉ።
እንደማሳያም ሰሞኑን የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያና የባሃርዳር ከንቲባን ጨምሮ አብዛኛውም አመራር የሚለጥፈው የልማት ጉዳይ ብቻ ነው በሚል ያቀርባሉ።
ይሄንን ማድረግ ያስፈለገው ደግሞ አሁን ላይ ሁሉም አይኑንና ብእሩን ኦህዴድ በአማራ ክልልና ህዝብ ላይ እየፈጸመ ባለው ወንጀል ላይ በማድረጉ ነው ይላሉ።
እናም ይሄን አጀንዳ ለመቀልበስና የህዝቡን ልብ ለመክፈል አመራሩም ሆነ መገናኛ ብዙሃኖቻቸው ትኩረታቸውን በልማትና መሰል ጉዳዮች ላይ እንዲያደርጉ ቤተመንግስቱን ከተቆጣጠረው ግለሰብ ትእዛዝ መሰጠቱን ገልጸዋል።
አሁን ላይ የብአዴኑ ጥቅመኛ ስብስብ ህዝባዊ ትግሉን ለመጎተትና አማራውን ለማስበላት ያለውን አቅም ሁሉ እየተጠቀመ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በተለይ ደግሞ ከላይ ካለው ጀምሮ እስከ ታችኛው እርከን ያለው የብአዴን ስብስብ በጥቅም የተሳሰረ መሆኑ ደግሞ ነገሩን አክፍቶታል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል።