በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ እንዲሁም በሸበል በረትታና በደጀን በረሃዎችም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል ገብቶ ተኩስ መክፈቱን የሕዝባዊ ሃይል አባላቱን ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ወደ አካባቢው ሃይሉን ማጋዙን አላቋረጠም የሚሉት አባላቱ እስከ ገጠሩ ክፍል ድረስ ሃይሉን እያስገባ መሆኑን ይናገራሉ።
ይሄ ቡድን በፋኖ ህዝባዊ ሃይል ብቻ ሳይሆን የንጹሃን ዜጎችንም ፈተና አብዝቶታል ብለዋል።
ኢትዮ 360 ባለፈው ሳምንት ባወጣው መረጃው የብአዴኑ ስብስብ ሁለተኛ መንግስት ሊያወጅብኝ ነው በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይል እንዲገባለት እየተማጸነ ነው መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
በሸበል በረንታና በደጀን በረሃ በኩልና በተለያዩ አቅጣጫዎች ከፍተኛ ቁጥር እያጋዘ ያለው የኦህዴዱ ስርአት ለከሃዲው ብአዴን ምላሽ ለመስጠት ነው ይላሉ።
ይሄው ከፍተና ቁጥር ያለው የኦህዴድ ሃይልም ወደ በረሃ የገባውን የፋኖ ህዝባዊ ሃይልን ለመክበብ ጥረት እያደረገ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ይሄ አዲስ ስምሪት ይዞ የሚመጣው ሃይል በዋናነት እየተመራ የሚጓዘው ደግሞ ከክልሉ የጸጥታ ሃይል ጋር በመሆን ነው ይላሉ።
ይሄው የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል ከፊት አስቀድሞ የሚመጣው ሆዳሙን ካድሬ ነው ይላሉ።
ኢትዮ 360 በትላንት የዛሬ ምናለ የቀጥታ ስርጭቱ አዲሱ ዘመቻ የክልሉም ሚሊሻ፣ፖሊስና አድማ ብተና ከፊት በማስቀደም የሚካሄድ ነው በሚል መረጃውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
እናም በብአዴኑ የሆዳሞች ስብስብ እየተመራ የሚመጣው የኦህዴዱ ጦርም ዋነኛው ጥቃት ፈጻሚ ነው ብለዋል።
በጎጃም የተለያዩ አቅጣጭዎች እየተደረገ ያለውን ከበባ ሌላው የአማራ አካባቢ ማህበረሰብና ህዝባዊ ሃይሉ ሊያከሽፈው ይገባልም ብለዋል።
አሁን ላይ ጎጃም ላይ የተጀመረው ከበባ ነጥሎ የመምጣት ስትራቴጂ ነውና ሁሉም በጋራ ሊከላከለው ይገባል ሲሉ በኢትዮ 360 በኩል ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለው በሰሜን ሸዋ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ሙሉየለት ጭንቅሎ ደግሞ በየክፍለ ከተማው ፓሊስና ሚኒሻውን አስጠርንፎ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የሚመስል ልብስ እንደለብሱ በማስገደድ ላይ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል።
ያንን ከለበሱ በኋላም በየመንደሩ በሰልፍ ተሰልፈው ህብረተሰቡ እንዲያስፈራሩ መመሪያ እያወረደ መሆኑንም አመልክተዋል።
በዚህ መመሪያ መሰረትም በየክፍለ ከተማው በሚገኙ ሆድ አደር ካድሬዎች አማካኝነት መንደር ለመንደር ሲሽከረከሩ ይውላሉ ብለዋል ምንጮቹ።
ይሄንን መመሪያ ሰጭውና ህብረተሰቡ እንዲታመስ እያደረገ ያለው የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ሙልዬለት ጭንቅሎ ከመከላከያ አዛዥ ፣ ከፌደራል ፓሊስ አዛዥ እና ከዞን ካቢኒዎች ጋር በመሆን በኩኬለሽ የነበረውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሲያቀናብር የነበረው እሱ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።