በደቡብ ኦሞ ጂንካን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጅ የሆኑ መከላከያ አባላት በተለ እስር ቤቶች ታፍነው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ጅንካን ጨምሮ በሐዋሳ፣በአርባምንጭና በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙት እነዚህ የሰራዊቱ አባላት የአማራ ተወላጆችና ባለማእረጎች ሁሉ ያሉበት ስብስብ መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ስም ዝርዝራቸንና የታሰሩት የሰራዊቱ አባላት የላኩትን ደብዳቤ በማሳየት ችምር የሚናገሩት ቤተሰቦቻቸው ለመታሰራቸው ደግሞ የተለያየ ምክንያት እንደተቀመጠላቸውም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ነገር ግን ዋናው ምክንያት በአማራ ክልል ለተጀመረው እንቀስቃሴ ለወገኖቻቸው መረጃ ይሰጣሉ በሚል መሆኑንም ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።