ኢትዮጵያ ለነዳጅ ጭነት የምትገለገልባቸው ሁለት መርከቦች በኦህዴዱ አገዘዝ ለሲንጋፖር መንግስት መሸጣቸውን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገለጹ።
ባህርዳርና ሐዋሳ የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ሁለት መርከቦች ለሲንጋፖር ለሽያጭ መቅረብ ብቻ ሳይሆን የሰቀሉት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አለማ ወርዶ በሲንጋፖር አርማ እንዲተካ መደረጉንም ገልጸዋል።
የነዳጅ ጫኝ መርከቦቹ ስም የተቀየረ ሲሆን ለአንዱ መርከብ ሲቼ የሚል ስያሜ እንደተሰጠውም የውስጥ ምንጮቹ ተናግረዋል።
እነዚህ መርከቦች ለሽያጭ ከመቅረባቸው በፊት አባይ የተባለውን የነዳጅ ጫኝ መርከብ አየር በአየር ተሽጦ በስሙ ተመሳሳይ መርከብ አባይ ሁለት የሚል በግዢ ይሁን በኪራይ እንዲመጣ መደረጉን አጋልጠዋል።
መርከቦቹ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2012 ለነዳጅ ጭነት በሚል ከቻይና በህወሃት ዘመን የተገዙ መሆኑን ያስታውሳሉ።
እነዚህ መርከቦች በወቅቱ ሲገዙ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራትና ለቀጠናው ነዳጅ በማመላለስ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስገባሉ በሚል እንደነበርም አስታውሰዋል።
ነገር ግን አሁን ላይ በከፍተኛ የገንዘብ እጦት እየተሰቃየ ያለው የኦህዴዱ ስብስብ ቀጣይ እቅድ በአብያተ ክርስቲያናትና በመስኪዶች ውስጥ ያሉ ንዋየ ቅድሳትንና ቅርሶችን ለመዝረፍና ለሽያጭ ማቅረብ ነው ሲሉ የውስጥ ምንጮቹ አጋልጠዋል።
ኢትዮ 360 ሰሞኑን ባወጣው መረጃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት ካርጎን ጨምሮ በህወሃት ጊዜ የተሰሩ ትልልቅ ተቋማትን ሁሉ ለሽያጭ ለማቅረብ ቡድን መቋቋሙንና ስራው መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የህዝብ ተቋማት ለሽያጭ የሚቀርቡት ሃገሪቱ የገጠማትን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ ሳይሆን ለአንድ ግለሰቡ ተብሎ የሚሰራውን ቤተመንግስት ግንባታ ለማፋጠን መሆኑን ኢትዮ 360 በመረጃው ማጋለጡ ይታወቃል።
Комментарии