top of page

ሰኔ 7/2015 በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ እና የግል ቤቶች ግብር ክፍያ ከአንድ ወር በኋላ የ2016 ክፍያ እንደሚጀመር ተገለጹ።



በአዲስ አበባ አሁን ክፈሉ እየተባለው ያለው የጋራ መኖሪያና የግል ቤቶች ግብር ክፍያ ከአንድ ወር በኋላ የ2016 ክፍያ እንደሚጀመር የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገለጹ።



አሁን ህብረተሰቡ ክፈል በሚል እየተጠየቀ ያለው የ2015 መሆኑን ነው የውስጥ ምንጮቹ የሚናገሩት።



ነገር ግን በአንድ ወር ልዩነት የ2016 ግብርን አምጣ ለማለት የተዘጋጀው የኦህዴዱ ስብስብ የመክፈያ ጊዜውንም ከነሐሴ 2015 እስከ ጥቅምት 2016 የሚጠናቀቅ በሚል መመሪያ ማውረዱንም ተናግረዋል።


የአሁኑን ግብር መክፈል አቅቶት ግራ የገባው ነዋሪ በአንድ ወር ልዩነት ትከፍላለህ የተባለውን ግብር ከየት አምጥቶ እንደሚከፍል ማሰብ ከባድ ነው ይላሉ።




እንደ አሰራሩ ከሆኑ በትክክል የግብር መክፈያ ወቅት የአመቱ መጨረሻ ላይ መሆኑን ያነሳሉ።


ነገር ግን በልቼው ልሙት በሚል ሒሳብ ህዝብን ባዶ ለማስቀረት እየለፋ ያለው አካል የነዋሪውን ህይወት በመከራ ሞልቶታል ብለዋል።


የቤት ግብር ተብሎ እየተካሄደ ያለው ዘረፋ ከክፍል ክፍለ ከተማ እንደሚለያይም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በአንዳንዱ ክፍለ ከተማ ለመሃንዲስ በሚል ነዋሪው አንድ ሺ ብር እንዲከፍል ሲደረግ በአንዳንዱ ክፍለ ከተማ ደግሞ ክፍያው ወደ 500 ብር ዝቅ እንደሚል የውስጥ ምንጮቹ አስቀምጠዋል።


ሌላው አስገራሚ ነገር ይላሉ የውስጥ ምንጮቹ ከአዲስ አበባ ዘርፈዉ የወሰዷቸዉ ቀበሌዎች ጭራሽ የአከራይ ተከራይም ሆነ ግብር እንዳይከፍሉ የሚል መመሪያ እንደወረደላቸው ገልጸዋል።



ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ የተጫነበትን ግብር ክፈል ብቻ ሳይሆን ግብሩን እንዲያስከፍሉት የተመደቡት ሰዎች እንዲመጡለት የተደረገው ከገላን፣ከዱከምና ከሌሎች አካባቢዎች መሆኑን ተናግረዋል።


ግብር አስከፋይ በሚል የመጡት እነዚህ ግለሰቦች ማንበብ የማይችሉ በመሆናቸው ባለጉዳዩ ራሱ እያነበበላቸዉ ስራውን እየሰሩ መሆኑንም በአግራሞት ይገልጻሉ።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page