አርበኛ ዘመነ ካሴን ትላንት ለማፈንና ለመግደል ሞክሮ ያልተሳካለት አካል ዛሬ ከብርሸለቆና ከመኮድ ያመጣውን ሃይል በአካባቢው አሰማርቶ መጨረሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ትላንት በአንድ አቅጣጫ ቦምብ በማፈንዳት ወደ ግቢው ለመግባት የሞከረው አካል በመጣበት እንዲመለስ ቢደረግም አሁንም ግን ተጨማሪ ሃይሉን ለሌላ ጥቃት ማሰማራቱን ነው የሚናገሩት።
ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ በስብሰባ ችምር የኦህዴዱ ገባይ ቡድን ዘመን በምን መንገድ መገደል እንዳለበት እቅድ ሲያወጣ መቆየቱንና ከእቅዱ አንዱም ዘመነን ከእስር መልቀቅና በግርግር እንዲገደል ማድረግ መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
አሁን ዘመነ ላይ እየተደረገ ያለው ነገርም ይሄው ነው ሲሉ ምንጮቹ አስምረውበታል።
አርበኛ ዘመነ ካሴም ለህዝብ ባስተላለፈው መልእክት ላይ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንደማይሸሽና ህብረተሰቡም ምን ማድረግ እንዳለበት በግልጽ ማስቀመጡን አንስተዋል።
የባህርዳር ከተማም ሆነ ከተለያየ አቅጣጫ ተሞ አካባቢው ላይ የደረሰው ህዝብም ለሊት ሳይበግረው አርበኛውን ከቦ ማደሩን ነው ምንጮቹ ያመለከቱት።
አሁን ህዝቡ በተጠንቀቅ ባለበት ሆኖ እየተጠባበቀ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮቹ ምናልባትም ምሽት ላይ ሌላ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
የገዳዩ ቡድን ስብስብ አሁን ላይ ነገሮች የበረዱና ምንም እንደሌለ ለማስመሰል ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ቢሆንም ህዝቡ ግን ካለበት ነቅነቅ ባለማለት እቅዱን በማክሸፍ ላይ ነው ብለዋል።
ትላንት ምሽት ከአራት ሰአት ጀምሮ በአርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ የተደረገው የመግደል ሙከራ ሁሉም የባህርዳር ወጣትና የአካባቢው ነዋሪ ወደ አርበኛው መኖሪያ በመትመም አርበኛውን መታደግ ቢችልም አሁን ግን ይሄው ገዳይ ቡድን አካባቢውን ወሮ እንደሚገኝ ይናገራሉ።
ከፍተኛ ቁጥር ያለውና የመከላከያ ልብስን ከለበሰው የኦነጉ ስብስብ ሌላ የመከላከያን ልብስ እንዲለብሱ የተደረጉ የአማራ አድማ ብተና፣ፖሊስና ሚሊሻ የሚባሉ ሆድ አደር ስብስቦችም የራሳቸውን ወገን ለመግደል አብረው መሰለፋቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
Comments