top of page

ሰኔ 8/2015በወላይታ ሁሉም አካባቢው በፌደራል ሃይል እንዲከበብ መደረጉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



በወላይታ ምርጫ እናካሂዳለን በሚል ሰበብ ሁሉም አካባቢው በፌደራል ሃይል እንዲከበብ መደረጉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



ይሄ ከበባም ይካሄዳል የሚባለው ምርጫ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይቆያል ቢባልም ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ይሄ ሃይል በሰላም ስለመውጣቱ ግን በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም ሲሉ ሁኔታውን ይገልጻሉ።



ዛሬ ከማለዳው ጀምሮም ይሄ የፌደራል ሃይል የደቡብ ልዩ ሃይልን ጨምሮ የዞኑን ወረዳዎችና ቀበሌዎች ብሎም የከተማ አስተዳደሮች እስከ ገጠር ቀበሌዎች ድረስ እንዲወረሩ ማድረጉን ሳይጠቁሙ አላለፉም።



የመጀመሪያውን ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ሞክሮ የነበረው አካል በህዝብ እምቢተኝነት ሳይስካለት ቢቀርም አሁን ደግሞ ሃይል በማሰማራትና በማስገደድ ለማስፈጸም ስራውን ጀምሯል ይላሉ።



በመጀመሪያው ዙር ላይ የህዝብን እምቢተኝነት እንደጥሩ አጋጣሚ የወሰደው የካድሬው ስብስብ ስልጣኑን ሁሉ በህገወጥ መንገድ ለመቀራመት ቢሞክርም ከህዝብ ግን ሊያመልጥ አልቻለም ሲሉ ሁኔታውን ያስቀምጣሉ።



አሁንም ህዝብን በማስገደድ ህዝበ ውሳኔ አደርጋለሁ ብሎ የሚያስበው የኦህዴዱ ስብስብ ወላይታን ከዳር እስከ ዳር በሰራዊት እንድትከበብ አድርጓታል ይላሉ።



ከዛሬ ጀምሮ የዞኑ መደበኛ ፀጥታ መዋቅር በኮማንድ ፖስት እንዲመራ ቤተመንግስቱን ከተቆጣጠረው አካል የወረደውን ውሳኔ ተግባራዊ ያደረገው አካል ውሳኔው እንዳይቀለበስ ደግሞ ህዝብን ማፈን ጀምሯል ብለዋል።



አስገራሚው ነገር ይላሉ ምንጮቹ ፈርሷል በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲነገርለት የነበረው የደቡብ ልዩ ሃይልም ከነመለዮው ዛሬ ላይ በይፋ በዚሁ የአፈና ተግባር ላይ እንዲሰማራ መደረጉን ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page