በምስራቅ ጎጃም ደምበጫ ነገሮች ከሚታሰበው በላይ እየከረሩ መምጣታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ።
የአካባቢው ሽማግሌዎችም የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል ከአካባቢው እንዲወጣ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ ግን ሊያገኙ አለመቻላቸውንም አመልክተዋል።
ይሄንን ተከትሎም በደንበጫ ህዝብና በኦነጉ የመከላከያ ሃይል መካከል ያለው ፍጥጫ አሁንም መቀጠሉን ይናገራሉ።
ይሄው ገዳይ ቡድን ወደ አካባቢው መግባቱን ተከትሎ በንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በከፈተው ተኩስ በትንሹ 10 የሚሆኑ ንጽሃን ዜጎችን መግደሉን ኢትዮ 360 በመረጃው ማውጣቱ ይታወሳል።
የደንበጫና የአካባቢው ህዝብም ንጹሃንን ለመግደል የገባው ሃይል ቀያችንን ለቆ ካልወጣ ወደቤታችን አንመለስም በሚል ከተማውን እየጠበቀ መሆኑንም ነው ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ ያሰፈሩት።
የገዳይ ቡድኑ ስብስብ ደግሞ የማህበራት እህል ማከማቻ የሆነው መጋዘን ወደ ካምፕነት ተጠቅሞ ራሱ አደራጅቶ መቀመጡን ጠቁመዋል።
ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ውጡልን ቢላቸውም ያስገባን የከተማ አመራሩ ስለሆነ እሱ ውጡ ሲለን ነው የምንወጣ ቢሉም አመራር የተባለው አካል ግን እስካሁን ወደ አካባቢው አለመድረሱን ተናግረዋል።
በተደጋጋሚ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ጥያቄ ሲያነሱለት የቆዩት የአካባቢው ሽማግሌዎችም ዛሬ እስከ ቀኑ አስር ሰአት ድረስ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ ማሳለፋቸውንም ሳይጠቁሙ አለላፉም።
ይሄ ውሳኔን ተከትሎ ገዳዩ ቡድን ከአካባቢው ካልወጣ በቀጣይ የሚወሰነው ውሳኔ ባይታወቅም የአካባቢው ማህበረሰብ ግን አሁንም አካባቢውን ከቦ እየተጠባበቀ መሆኑን ነው ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ ያሰፈሩት።
Comments