top of page

ሰኔ 8/2015 የህዳሴው ግድብ የውሃ ከፍታን የሚናገሩ ቁጥሮች እንዲጠፉ እየተደርጉ መሆኑን ተገለጹ።



የህዳሴው ግድብ የውሃ ከፍታን የሚናገሩ ቁጥሮች በቀለም እንዲጠፉ እየተደርጉ መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገለጹ።



ይሄ እየተደረገ ያለው ደግሞ ሰሞኑን ከህዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ አዲስ ለሚጀመረው ፕሮፓጋንዳ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።



ከህዳሳው ግድብ ውሃ ሙሌትም ሆነ ከተርባይኖች መቀነስ ብሎም ከአጠቃላዩ ግንባታ ጋር ታያይዞ በተለያየ ጊዜ የተሳሳተ መረጃ በማውጣት የሚታወቀው የኦህዴዱ ስብስብ አሁን ደግሞ ወደ ቁጥር ድበቃ ተሸጋግሯል ብለዋል።



ባለፉት አመታት የህዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌትን በተመለከተ የተለያዩ ቁጥሮች ሲነገሩ መቆየታቸው ይታወቃል የሚሉ የውስጥ ምንጮቹ ምናልባትም አሁን ላይ የቁጥር ቅሸባ ያስፈለገው አንድም የህዳሴን ግድብ ለመሰልቀጥ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት አልያም ደግሞ ከግብጭ ጋር የተደረሰውን ውስጣዊ ስምምነት ለማስፈጸም ነው ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።



ለህዳሴው ግድብ ከህዝብ የተዋጣውን ገንዘብ ለቤተመንግስት ግንባታ በሚል ሊሰርቅ የተዘጋጀው አብይ አህመድ አሁን ደግሞ የውሃ ሙሌት ቁጥር ስርቆት ላይ ተሰማርቷል ሲሉ የውስጥ ምንጮቹ ይናገራሉ።



ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያሉ እውነተኛ መረጃዎች እንዳይወጡ አስቀድሞ ኢንጂነር ስመኘውን ያስወገደው የኦህዴዱ ስብስብ አሁን ላይ የህዝብ ሃብት የሆነውን ግድብ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ቀን ከሌት እየሰራ ነው ሲሉም በመረጃቸው አስቀምጠዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page