በቤንሻንጉ መተከል ዞን የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩ አመራሮች በድርድር ስም ወደ ቀድሞ ስልጣናቸው እንዲመለሱ እየተደረጉ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምና ከቀያቸው ሲፈናቀሉ ዋና አስገዳይና አፈናቃይ የነበሩት አመራሮች ዛሬ ወደ ስልጣናቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል ብለዋል።
ከነዚህም መካከል ለሜሳ ዋውያና ጊሳ ዚፋህ እንደሚገኙበትም በማሳያነት ያቀርባሉ።
የመተከል ዞን አስተዳዳሪ የነበረው ለሜሳ ዋውያ በቡለን ወረዳ በተጨፈጨፉ አማራዎች ተከሶ ማረሚያ የነበረ ግለሰብ መሆኑን ያነሳሉ።
ዛሬ ግን የሰራው ወንጀል ሁሉ ወደ ጎን ተብሎ ከማረሚያ እንዲወጣና በቀጥታ ወደ ዞን አስተዳዳሪነት ቦታው እንዲመለስ ተደርጓል ብለዋል።
የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ የነበረው ጊሳ ዚፋህ ደግሞ በ2011ዓ.ም በመተከል በነበረው ጭፍጨፋ ተከሶ ነበር ይላሉ።
ከ3አመት እስር በኋላ ግን ወንጀሉ ወደ ጎን ተብሎ የግብርና ቢሮ መምሪያ ሀላፊ ሆኖ እንዲሾም ሆኗል ብለዋል ምንጮቹ።
በመተከል ጭፍጨፋ ሲፈፅሙና ሲያስፈፅሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩ አመራሮች በድርድር ስም ከእስር ተለቀው ወደ ስልጣናቸው እየተመለሱ ነው ይላሉ።
ምናልባትም እነዚህ ገዳይና አስገዳይ የነበሩ አመራሮች ወደ ስልጣናቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለው ሌላ ዙር የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም የተያዘውን እቅድ ለማስፈጸም ይሆናል ሲሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
Comments