top of page

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ እና አካባቢው ከነገ ጀምሮ ጦርነት ለመጀመር የኦህዴድ ጦር የመከላከያ ዩኒፎርም ለብሶ መዘጋጀቱ ተገለፀ።

(ኢትዮ 360 -ሚያዚያ 11/2015)በአማራ ክልል በሸዋና አካባቢው ከነገ ጀምሮ ጦርነት ሊከፍተ የተዘጋጀው የኦህዴዱ መከላከያ በሸዋሮቢት ትልልቅ ምሽጎችን ሲቆፍር በማጀቴ ደግሞ ፋኖዎችን ትጥቅ ለማስፈታት አዲስ ከበባ እያደረገ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ። ይሄንን ለማሳካት በተለያዩ አቅጣጫዎች የመከላከያ ልብስብ በማልበስ የኦነግ ገዳይ ቡድንን ወደ ክልሉ እያጋዘ ያለው የኦነጉ አገዛዝ ከቆቦ እንዲነሳ ያደረገው ሃይል አሁን ላይ ደሴን ተሻግሮ ኮምቦልቻ መድረሱንም አመልክተዋል። በተለይ ሸዋ ላይ ያለውን የፋኖ ህዝባዊ ሃይልንም ሆነ የልዩ ሃይሉን ብሎም የማህበረሰቡ ትጥቅ አስፈታለሁ ያለው ይሄው ቡድን ይሄንን ማድረግ ካልቻለ ደግሞ ምናልባትም ነገ በግልጽ በአካባቢው ጦርነት ሊከፍት ይችላል ሲሉም ያለውን እውነታ አስቀምጠዋል።



ይሄ ቡድን ሰሞኑን የፋኖ ህዝባዊ ሃይሉንም ሆነ የልዩ ሃይሉን መረጃ ካሰባሰበ በኋላ ሁሉንም በአንድ ላይ እንጨርሳለን በሚል ተዘጋጅተው የነበሩት እነብርሃኑ ጁላ ከባድ ውርደትን እንዲከናነቡ ሆነዋል ብለዋል። በዚህ የተበሳጨው የነብርሃኑና የነአብይ ቡድን ጀቶችን ጨምሮ ታንኮጭና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን ወደ ጎንደር ሲያግዝ መታየቱንም ያነሳሉ። ይሄን ሁሉ መሳሪያ ወደ አካባቢው እየላከ ያለው የኦህዴዱ ስብስብ በጎን በኩል ደግሞ አርበኞቹን ለማንበርከክ ሽማግሌ ለመላክ እየሞከረ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም። የኦህዴዱ ሃይል ክልሉ ላይ የተዘጉበትን መንገዶች ሁሉ ሰብሮ ለመግባት ተዘጋጅቷል የሚሉት ምንጮቹ ለዚህ ደግሞ የአማራ ልዩ ሃይልና የህዝባዊ ሃይሉ ፋኖ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ይሄንን ቡድን በመጣበት እንዲመለስ ሊያደርጉት ይገባል ብለዋል።



Recent Posts

See All

ነሃሴ 18/2015 በሰሜን ሸዋ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

በሰሜን ሸዋ አንፆኪያ /መኮይ/ ገና በጠዋቱ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ። ገና ሳይነጋ ንጹሃንን ሊፈጅ ወደ በአንጾኪያ...

ነሐሴ 18/2015 የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ገለጹ።

በደቡብ ክልል አዲስ ተመሰረተ በተባለው ክልል ውስጥ ያሉው የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ። አዲስ ተቋቋመ በተባለውና ከፍተኛ ቁጥር...

Comentários


bottom of page