(ኢትዮ 360-ሚያዚያ 25/2015)በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ከመቼው በከፋ መልኩ አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና የደቡባዊ አፍሪካው ሚዲያ ኢንስቲትዩት በጋራ ያወጡት የዳሰሳ ጥናት አመለከተ።
በጋራ የወጣው የዳሰሳ ጥናት ባለፈው የፈረንጆቹ አመት ብቻ 29 ጋዜጠኞችን ወደ እስር ያጋዘው ስርአት የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን ከመቼው ጊዜ በከፋ መልኩ ለአደጋ አጋልጦታል ብሏል።
ባለስልጣናት የፕሬስ ነጻነትን ማፈን በሚፈልጉባቸው በምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት፤ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ጨምሯል ሲሉ አመልክቷል።
ተቋማቱ ይሄንን የዳሰሳ ጥናት ይፋ ያደረጉት ዛሬ ታስቦ የሚውለውን የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን በማስመልከት ነው።
ዳሰሳው የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን በሌሎች 9 አፍሪካ ሀገራት ያለውን የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን እና በጋዜጠኞች ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በማሳያነትም አስቀምጧል።
እንደ ዳሰሳው ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን በማሰር ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ቀጥሎ ስሟ የተቀመጠው ኢትዮጵያ መሆኗንም ይፋ አድርጓል።
Comments