top of page

በደብረብርሃን ከተማ መንግስት ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራው አካል ግልጽ ጦርነት ከፍቷል

(ኢትዮ 360-ሚያዚያ 3/2015)


በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከተማ መንግስት ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራው አካል በግልጽ ጦርነት ከፍቷል ሲሉ ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ። ጠዋት ላይ በጫጫ መስመር የገባው የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል ግልጽ ጦርነት ከፍቷል ብለዋል።

ከከተማ በአንድና ሁለት ኪሎ ሜትር ርቅት ላይ ሆኖ ከባድ መሳሪያ በመጥመድ ጦርነት የጀመረውን አካል የልዩ ሃይሉና የፋኖ ህዝባዊ ሃይል የዚህን ቡድን ጥቃት ለመከላከል እየጣሩ መሆኑን ይናገራሉ። ኦዳ ላይ ካምፑን የገነባው ይሄው ገዳይ ቡድን የአዲስ አበባን መንገድ ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ነው ጉዳት እያደረሰ ያለው ይላሉ።

ባለው ሃይል ጦርነቱን መግፋት ያልቻለው ገዳይ ቡድን ተጨማሪ ሃይል እያጋዘ መሆኑንም ነው ያስቀመጡት። አሁንም በከተማው ያለው የህዝብ ማእበል እንደቀጠለ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ እናቶች ደግሞ ለልጆቹ ምግብ በማቅረብ ላይ ነው ይላሉ።ይሄ እየሆነ ባለበት ሰአት ግን የክልሉ ፖሊስና ሚሊሻ የሚባለው ስብስብ ገዳይ ቡድኑን በር ከፍቶ በማስገባት ወገኖቹን እያስጨረሰ ነው ሲሉ በሃዘኔታ ይናገራሉ።

ትልቅ ከተማ በሆነቸው ደብረብርሃን የተጀመረውን የዚህ ገዳይ ቡድን እንቅስቃሴ ለማስቆም በሽምግልና ስም የመጡ ሰዎች ቢኖሩም ሰሚ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ይላሉ። አጣዬን መነሻ አድርጎ የመጣው ሃይል ዋና አላማው ህዝብን ማጥፋት ነው የሚሉት ነዋሪዎች አሁን በትክክል መንግስታዊ ጦርነት መከፈቱ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በባህርዳር አባይ ማዶ የፈንዳው ቦንብ ዋናው ተጠያቂ የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል ነው ሲሉ የአይን እምኞች ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።እነሱ እንደሚሉት ይሄው ቡድን በፓትሮል ባለፈ በ3 ደቂቃ ልዩነት መፈንዳቱ አንዱ ማሳያ ሲሆን የተጎዱትን ለማዳን ሲረባረብ የነበረውን ህዝብ በጥይት ሲመታ የነበረው ይሄው ቡድን መሆኑን ደግሞ በዋናነት ተጠያቂ መሆኑን ማሳያ ነው ሲሉም ያስቀምጣሉ።


ነገር ግን የኦህዴዱ ቡድን በከተማ ውስጥ እያደረገው ካለ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የግሮሰሪ ባለቤቶችም ሆኑ ወጣቶች ወደ እንደዚህ አይነት ስፍራ እንዳይሄዱና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተደጋጋሚ ጥቆማ ሲሰጥ መቆየቱን ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comentarios


bottom of page