top of page

ነሀሴ 11/2015በአሰላ ከተማ የብልፅግና ካድሬዎች የብሔር ግጭት ለማስነሳት ከፍተኛ የሆነ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው !


በአሰላ ከተማ የብልፅግና ካድሬዎች የብሔር ግጭት ለማስነሳት ከፍተኛ የሆነ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ።


ይሄንን እቅድ ለማሳካት ደግሞ ሰሞኑን አማርኛ ተናጋሪ እና አማራ ተወላጆችን ለብቻ መምህራን ኮሌጅ ማሰልጠኛ ውስጥ ሰብስበው ሲሳደቡና ሲያስፈራሩ መክረማቸውን ይናገራሉ።


በዚሁ መድረክ ላይ ለተሰበሰበው የአማራ ተወላጅ አማራ የሚኖረው እኛ ስንፈቅድለት ብቻ ነው በሚል ሲዝቱ እንደነበርም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


የአማራ ተወላጅ የሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትን ፋኖን ትረዳላችሁ ስለዚህ እናንተንም ቤተሰባችሁንም አስረን ሀብት ንብረታችሁን እንወርሳለን የሚለው ማስፈራሪያም ሲሰነዘር የነበረው ከዚሁ ስብሰባውን እመራለሁ ከሚለው ቡድን ነበር ሲሉም ምንጮቹ አመልክተዋል።በመድረኩ ላይ መርዛቸውን ሲረጩ የነበሩት የገዳዩ ቡድን ስብስቦች ለስብሰባ የተጠራውን የአማራ ተወላጅ በከፍተኛ ሁኔታ እያስፈራሩ የብሔር ግጭት ለማስነሳት ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ነው ሲሉም ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።


የከተማውን ነዋሪም አፍሰን እናስራለን በሚል ከባድ ውጥረት መንገሱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ተወላጆችን ለብቻ ስብሰባ የጠራው ይሄው ቡድን ነፍጠኛ ሀብት ንብረታችሁን ወርሶ ሊገዛችሁ ነው እና የኦህዴዱን አገዛዝ ማንኛውም የኦሮሞ ሕዝብ ልትደግፉት ይገባል በሚል የተሳሳተ ትርክት ሲያቀርቡ መዋላቸውን አንስተዋል።


ይሄን ካላደረጋችሁ ደግሞ አማሮች እንደ ድሮዎ ሊገዟችሁና መሬታችሁን ወስደው ባሪያ ሊያደርጓችሁ ስለሆነ የትኛውም ኦሮሞ ከአማራ ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥ አለበት የሚል ቁርጥ መመሪያ ማስተላለፋቸውንም አመልክተዋል።


ከስብሰባው በኋላም በየመንደሩ እየዞረ በጅምላ ልናስራችሁ ነው በሚል የሚያስፈራራው አካል ደግሞ ከተማዋን ሰላም እንዲርቃት ህዝቡም በጭንቀት እንዲሞት እያደረገ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ለኢትዮ

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Comments


bottom of page