ነሀሴ 9/2015
የፖለቲከኛው የአቶ ልደቱ አያሌው መኖሪያ ቤት ዛሬ በሰው በላው ስርአት ሃይሎች ሲበረበር መዋሉን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ደብረዘይት የሚገኝው መኖሪያ ቤቱ የተበረበረው በስምንት የፖሊስና የልዩ ሃይል አባላት መበርበሩን ነው ምንጮቹ የሚናገሩት።
ቤቱን ሊበረብሩ የገቡት እነዚሁ ስብስቦች የሚፈልጉትን ማገነት ባለመቻላቸው ለረጅም ሰአት በቤቱ ውስጥ መቆየታቸውንም ሳይጠቁ አላለፉም።
ቤቱን ሲበረብር ከነበረው ቡድን መካከል የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ልብስን የለበሱ እንደነበሩበትም ምንጮቹ ይናገራሉ።
ከጠዋቱ አራት ሰአት አካባቢ በተደረገው በዚሁ ብርበራ ሁለት የአይን እማኞች ናቸው የተባሉ ግለሰቦችም አብረው እንደነበሩ ጠቁመዋል።
ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ይዘን መተናል ያለው ይሄውን ስብስብ ለቤቱ ጥበቃ ግን ማዛዣውን እንዲያነብ አልፈቀደለትም ብለዋል።
ፈታሽ ነኝ የሚለው ቡድን ለረጅም ሰአት ቤቱ ውስጥ ሲበረብር ጊዜውን ቢያጠፋም ከቤቱ ውስጥ ያገኘው ምንም ነገር ባለመኖሩ ባዶ እጁን ተመልሷል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።
Comentários