በዚህ የስራ ማቆም አድማ ላይ በዞን መዋቅር የሚገኙ የሁሉም መምሪያ መንግስት ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በስራ ማቆም አድማው ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የዱራሜ ከተማ አስተዳደር መንግስት ሰራተኞች እና የቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ሰራተኞችም ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመው ተቃውሞውን መቀላቀላቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።
በዞኑ ባሉ በሁሉም ከተማ እና ወረዳ መዋቅሮች የስራ ማቆም አድማ መደረጉን የኢትዮ 360 ምንጮች ከየስፍራው ባሰባሰቡት መረጃ አመላክተዋል።
በዞኑ በሁሉም አከባቢ አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎችም የስራ ማቆም አድማውን መቀላቀላቸውን ነው ምንጮቹ ገልጸዋል።
በዞኑ በሚገኙ በሁሉም አካባቢዎች ሆቴሎች እና ሱቆች ዝግ ናቸው ብለዋል ምንጮቹ።
ህዝቡ በዚህ መልኩ ተቃውሞውን ሲገልጹ ገዳዩ ስርአት ደግሞ በዞኑ የሚገኙ ሁሉም ከተሞች በዚሁ ገዳይ ቡድን ሃይል መወረራቸውን አመልክተዋል።
ተፈቅዶ የነበረው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍም በዚሁ ሃይል እንዲሰረዝ መደረጉ የበለጠ የህዝቡን ቁጣ አባብሶታል ብለዋል።
ሕዝባዊ ተቃውሞው በሁሉም የደቡብ ክልሎች እየተስፋፋ መሆኑንም ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።