top of page

ነሀሴ 9/2015 በ ፍኖተ ሰላም ከመቶ በላይ ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን በግፍ ያስጨፈጨፈው አስተኳሽ ተገደለ!
በጎጃም ፍኖተ ሰላም ከመቶ በላይ ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን በግፍ ያስጨፈጨፈው የድሮን አስተኳሽ በሰአታት ልዩነት ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገለጹ።በዛው በፍኖተ ሰላም በሚገኝ ሆቴል ተቀምጦ የሃዝባዊ ሃይሉን መውጫና መግቢያ ሲሰልል የነበረ የህወሃት አባል የድሮን አስተኳሽነትን ሃለፊነት ከገዳዩ ቡድን ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ይናገራሉ።ለኢትዮ 360 መረጃውን ያደረሱትና በድሮን ባለሙያነት ገዳዩን እያገለገሉ ያሉ ባለሙያዎች መረጃ ከሆነ ድሮኑ ድብደባ ለማካሄድ አስተኳሽ ማግኘት የግድ ይለዋል ሲሉ አሰራሩን ያናገራሉ።ድሮኑ ወደሚባለው አካባቢ ይሂድ እንጂ አስተኳሹ አቅጣጫ ካልሰጠው በቀር የድሮኑ ካሜራ ዝም ብሎ ሲዞር አይውልም ሲሉም የውስጥ ባለሙያዎቹ ለኢትዮ 360 ባደረሱት መረጃ ላይ አመልክተዋል።


በፍኖተ ሰላምም የሆነው ይሄው ነውስ ሲሉ ክስተቱን ይናገራሉ።


በወቅቱ የህዝባዊ ሃይሉን እንቅስቃሴ እንዲከታተል የተላከው የህወሃት አባል በአካባቢው በሚገኝ ሆቴል ውስጥ አድፍጦ ሲጠባበቅ መቆየቱን ይናገራሉ።


ወቅቱም ደርሶ ሰው በላው ስርአት የህዝባዊ ሃይሉን በቀጥታ እንዲመታ ለድሮኑ አቅጣጫ መስጠቱን ይናገራሉ።


እንዳለመታደል ሆኖ ግን የሰጠው አቅጣጫና ደቂቃ የህዝባዊ ሃይሉ አባላት በአካባቢው ያሉበት ሳይሆን ከቤተክርስቲያን የሚመለሱና በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ እንዲያርፍ ያደረገው ኢላማ ከ100 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን በግፍ እንዲጨፈጨፉ አድርጓል ባይ ናቸው።ግለሰቡ ሶስት መታወቂያዎችን ይዞ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በወቅቱን ይሄንን ግፍ ባስፈጸመ በሰአታት ልዩነት ውስጥ ባልታወቁ ሰዎች እቺን ምድር እንዲሰናበት ተደርጓል ብለዋል።


ንጹሃንን ለመግደል ከውጭ እየተጋዘ ያለውን ይሄንን መሳሪያ የሚተኩሱት የገዳዩ ቡድን ባለሙያዎች በትክክል አስተኳሽ ካላገኙና ቦታው ይሄነው ተብለው በካሜራ ማየት ካልቻሉ በቀር መምታት አይችሉም ሲሉም አሰራሩን ያስቀምጣሉ።


በዚህ መልኩ የአማራውን ህዝብ ለማስጨረስ በየአካባቢው የተሰማሩ የገዳዩ ስርአት ጆሮ ጠቢዎች መኖራቸውንም በግልጽ አስቀምጠዋል።


ባለሙያዎቹ ምናልባትም ህዝባዊ ሃይሉም ሆነ ማህበረሰቡ ከድሮኑ ጥቃት ራሱን ለመከላከል የሚችልበትንም መንገድ ለኢትዮ 360 በዝርዝር አድርሰዋል።


አሰቃቂ የሆነውን የድሮን ጥቃት ለመከላከል ከተቻለ የመጀመሪያው ስራ በህዝባዊ ሃይሉና በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነው መረጃ የሚሰጡ አስተኳሽ ኦፒዎችን በተቻለ አቅም አድኖ መያዝ አደጋውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስቀረት ያስችላል ይላሉ።


ሌላው መንገድ ደግሞ እንቅስቃሴያውቸውን ከለላ የሞሆኑ ነገሮችን በመጠቀምና ከመሬት ገፅ መመሳሰል የሚያስችሉ ዛፍና ቁጥቋጦን መጠቀም ተመራጭ ነው ይላሉ።


የአየር ሁኔታ ያገነዘብ እንቅስቃሴ በተለይ ደግሞ ዝናባና ዳመናማ የአየር ኔታን በተሽከርካሪ መጠቀምና ብሎም አሳሳች ምልክቶችን ወይንም ኢላማዎችን መጠቀም አደጋውን ለመቀነስ ጥሩ ዘዴ ነው ሲሉ ጥቆማቸውን ይሰጣሉ።


በተለይ ደግሞ የህዝባዊ ሃይሉ አመራሮች በተለይ ማስክ፣ መነፀር፣ ኮፍያ፣ ጥላ፣ ቋሚ የሞባይል ቁጥር አለመጠቀምጠ ከእይታ ለመሰወር መወሰድ ያለበት ዋና ጥንቃቄ ነው ሲሉም አስቀምጠውታል።


ያለመሪ የማይንቀሳቀሰውን የድሮን ቴክኖሎጂ አቅጣጫ ለማሳት ህዝባዊ ሃይሉ ተበታትኖ በመጓዝና ን ጥንቃቂ ማድረግ ዛፎች፣ ድልድዩችና ዋሻወችን በብዛት እንደመደበቂያ በመጠቀም የገዳዩን ስርአት አካሄድ ማስቆም ይችላሉ ሲሉም ለኢትዮ 360 ጥቆማውን አድርሰዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ትላንት ምሽት ሁለት ሰአት አካባቢ UAF1225(Emrate airforce 1225 ) ተብሎ በሚጠራ አይሮፕላን ሁለት ሄሊኮፍተር እና በርካታ ዘመናዊ መሳሪ ጭኖ የመጣው አይሮፕላን መሳሪያዎቹን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲያራግፍ ማየታቸውን የኢትዮ 360 የአይን እማኞች ገልጸዋል።


አውሮፕላኑ ቦሌ ከደረሰ በኋላ ጭኖት የመጣውን ገዳይ መሳሪያ ማንም እንዳያይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሲደረግ እንደነበርም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በትክክል ምን ያህል መሳሪያ ነው የሚለውን ማወቅ ባይቻልም ነገር ግን ከአውሮፕላኑ ሲወርድ የነበረው መሳሪያ በቁጥር ከፈተኛ መሆኑን ግን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Commentaires


bottom of page