top of page

ነሀሴ 9/2015 የዘር ማጥፋት ስራ ውስጥ የህዋሃት ሃይል አልተሳተፈም በሚል የወጣው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ምንጮች ገለጹ።



በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው የዘር ማጥፋት ስራ ውስጥ የህዋሃት ሃይል አልተሳተፈም በሚል የወጣው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።



በተደጋጋሚ ኢትዮ 360 በመረጃው ህወሃት በተለያዩ ግንባሮች ሃይሉን ማሰለፉንና የአማራ ንጹሃን ዜጎችን አብሮ እየፈጀ መሆኑን በተደጋጋሚ በመረጃው ማውጣቱ ይታወሳል።



ነገር ግን ህወሃት በአመራሮቹ በኩል በዚሁ ጦርነት ሃይሉን አለማሳተፉንና ነገር ግን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ከገዳዩ ስርአት ጋር እንደሚቆም በመግለጽ በማስቀመጥ ለዘር ማጥፋት ወንጀሉ ተባባሪ መሆኑን በቅርቡ ይፋ አድርጓል።



ነገር ግን አመራሩ ይሄን ይበል እንጂ ሃይሉን አማራ ክልል ድረስ በማስገባት ንጹሃንን ከመጨፍጨፍ ጀምሮ ከሰው በላው ስርአት መረጃው የሚያቀብሉ ወታደራዊ አመራሮችን ማሰማራቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ይናገራሉ።



አጠቃላይ የሕወሐትን የመረጃ ዘርፍ እየመራ ያለው ኮ/ል ተወልደ በድርድሩ ወቅት የነበረ ዋና ሰው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ የአማራን ጉዳይ እያጠናቀረ ቤተመንግስቱን ለተቆጣጠረው ገዳይ ቡድን የሚያቀብል ግልሰብ ነው ይላሉ ምንጮቹ።



በብሔራዊ መረጃ ሁመራ ተመድቦ የነበረውና ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ሲከበብ የሀምሌ አምስት ኦፕሬሽንን ከመሩት የህወሃት ሰዎች አንዱ ተከስተ የሚባለው የህወሃት ሰው መሆኑን ያስታውሳሉ።

ወልቃይት ጠገዴ ሰፍረው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን መልምሎ የደህንነት ስራ ያሰራ የነበረው ይሄው ግለሰብ እንደነበርም ይጠቁማሉ።


አሁን አማራ ላይ ደግሞ መረጃ አሰባሳቢ ሆኖ ቤተመንግስቱን ከተቆጣጠረው ገዳይ ቡድን ጋር እየሰራ ነው ሲሉ ምንጮቹ አጋልጠዋል።


ሲሳይ የተባለ በጌታቸው አሰፋ መዝገብ ተከስሶ የነበረው ገልሰብ ደግሞ በጎንደር መተማ የህወሓትን ደህንነት ስራ ሲያከናውን ቆይቶ አሁን ላይ ደግሞ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሳምሪ የተባለውን ገዳይ ቡድን ከሰው በላው ስርአት ጋር በመሆን ለሌላ ዙር ጭፍጨፋ ወደ አካባቢው እያስገባ መሆኑን ኢትዮ 360 በቅርቡ በመረጃው ማውታቱ ይታወሳል።


ገበረ ዮሐንስ የሚባለው የህወሃት ሰው ደግሞ የውጭ መረጃ ዳሬክተር በመሆን ያገለገለና በህወሓት የድሮው የጫካ ትግል ጎንደር እና ሁመራ በስለላ ስራ ተሰማርቶ እንደነበርም ያስታውሳሉ።


በለመደው ተግባሩ አሁን ላይ የአማራውን ጉዳይ እየሰለለ ለገዳዩ መሪ በማቀበል ላይ ነው ብለዋል።


ሜ/ር ጀነራል ገብሬ ዲላ ደግሞ የፌደራሊስት ሐይሎች በሚል በሐገር ደረጃ አዲስ ኃይል በማደራጀት እየመራ ያለ ብቻ ሳይሆን አማራን ይቃወማሉ የሚላቸውንና ኑሯቸውን በአማራ ክልል ያደረጉ ስብስቦችን እያደራጀና በአማራው እልቂት ላይ ዋና ተሳታፊ ሆኖ የሚገኝ ግለሰብ እንደሆነ አጋልጠዋል።


ከዚህም ሌላ በጦርነቱ ወቅት ከመከላከያ ሰራዊቱ የተቀነሱ የህወሓት አባላት በአማራ ክልል ንጹሃንን ለመጨረስ መሰማራታቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ባለፈው ጦርነት የተሳተፉት በርካታ የህወሓት ሐይሎችም በዚሁ የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ተሳታፊ ናቸው ሲሉም ምንጮቹ አመልክተዋል

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page